ሥሙ ፡ ሞገሳም ፡ ነው (Semu Mogesam New) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

እንኳን ፡ ማንነቱ ፡ ሥሙ ፡ ሞገሳም ፡ ነው
ወዶ ፡ አይደለም ፡ ፍጥረት ፡ ሰዎች ፡ የሚርበደበደው
ከወዲህ ፡ ተጠርቶ ፡ ከማዶ ፡ ይሰራል
ድንገት ፡ ደርሶ ፡ የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ ያሸብራል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ብርቱ ፡ ጉልበት ፡ አለበት
አይቻለሁ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሲመታ ፡ ሲያንቀጠቅጥ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው
በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

የበሽታ ፡ ብርታት ፡ የደዌ ፡ ጉልበት
አይፈልግም ፡ የጌታ ፡ ሥም ፡ እንዲጠራበት
በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ላይ ፡ የሚበረታው
ያውቃል ፡ ከተጠራ ፡ ሥሙ ፡ እንደሚነቅለው

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ታላቅ ፡ ጉልበት ፡ አለበት
አይቻለሁ ፡ ለህመሜ ፡ ሲሆን ፡ መድኃኒት (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው
በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

የመከራን ፡ ጭጋግ ፡ የሚችል ፡ መግፈፍ
በእውነተኛው ፡ በረከት ፡ የሚያትረፈርፍ
የባዶ ፡ ሸለቆ ፡ የመሙላት ፡ ሚስጥር
ሲጠራ ፡ ነው ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ በታላቅ ፡ ክብር

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሚለው ፡ ሥም ፡ ደግነትም ፡ አለበት
አይቻለሁ ፡ በጓዳዬ ፡ ሲሆንልኝ ፡ በረከት (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገው
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምም ፡ የተሰጠው
በሰማይም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በምድርም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከምድር ፡ በታች ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በሁሉ ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)