ሙሽራዪቱ ፡ ሆይ ፡ ተነሺ (Musherayitu Hoy Teneshi) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የልዑሉ ፡ አምላክ ፡ ማደሪያ
አካሉ ፡ የሆንሽ ፡ የእርሱ መኖሪያ
አንች ፡ ቤተክርስቲን ፡ ተነሺ
የሰጠሽን ፡ ተስፋ ፡ አትርሺ
ሁኝ ፡ እንጂ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ሙሽራ
ልትቆሚ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በተራራ
የሰርግሽ ፡ ቀን ፡ በጣም ፡ ቅርብ ፡ ነው
ሙሽራሽ ፡ ደጂ ፡ እያንኳኳ ፡ ነው

ዘምሪለት ፡ እንጂ ፡ በዕልልታ
የምን ፡ በራድ ፡ ትኩስ ፡ ለብታ
ድመቂ ፡ ንሺ ፡ ተቀደሽ
ሙሽራይቱ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ
መቅረዝሽ ፡ በዘይት ፡ ይሞላ
በር ፡ እንዳይዘጋብሽ ፡ ኋላ
ቀን ፡ ሳላ ፡ ዛሬ ፡ ተዘጋጂ
በፍጻሜው ፡ እንዳትጐጂ

ረሻሽ ፡ ወይ ፡ ጌታሽ ፡ መመለሱን
ጠብቂኝ ፡ እመጣለህ ፡ ማለቱን
መዘናጋቱ ፡ ምነው ፡ በዛ
ጣል ፡ እረግሽው ፡ ልክ ፡ እንደዋዛ
የወደፊቱ ፡ ክብር ፡ ተስፋ
ተጋረደ ፡ ከዓይንሽ ፡ ስር ፡ ጠፋ
ጊዜው ፡ ደርሷል ፡ እባክሽን ፡ ንቂ
ቤተክርስቲያን ፡ ተጠንቀቂ

ሊያደርግሽ ፡ ፍሬ ፡ አልባ ፡ ገለባ
የዓለም ፡ ኮተት ፡ ሰርጐ ፡ ገባ
ተኝተሽ ፡ ጠላት ፡ ዘሩን ፡ ዘራ
ምድርሽ ፡ እንክርዳድን ፡ አፈራ
በበጉ ፡ ደም ፡ ፈጥነሽ ፡ ታጠቢ
አስታውሺ ፡ ተስፋሽን ፡ አስቢ
የሰርጉ ፡ ቀን ፡ በጣም ፡ ተቃርቧል
ሙሽራሽ ፡ ወደ ፡ አንቺ ፡ ይመጣል

አሜን ፡ ማራናታ ፡ ቶሎ ፡ ና
የምትይበት ፡ ጊዜው ፡ ነውና
ይሰማ ፡ ድምፅሽ ፡ ያስተጋባ
ወደ ፡ ልዑል ፡ ማደሪያ ፡ ይግባ
ከእንግዲህ ፡ በምድር ፡ ምን ፡ ቀረሺ
ናፍቂ ፡ ወደሰማይ ፡ ገስግሺ
ይልቃል ፡ በዚያ ፡ ያለው ፡ ደስታ
ማሰማት ፡ ዝማሬና ፡ ዕልልታ

በዚያ ፡ እኮ ፡ ርሃብ ፡ ጥማት ፡ የለም
ደዌ ፡ ህመም ፡ አይታወቅም
እንባ ፡ ከዓይኖችሽ ፡ ይታበሳል
በጉ ፡ የአንች ፡ እረኛ ፡ ይሆናል
የበጉ ፡ መሽራ ፡ አንቺ ፡ ሆይ
ይህ ፡ ክበር ፡ አልናፈቀሽም ፡ ወይ
ይመጣል ፡ ወዳጅሽ ፡ ወደ ፡ አንቺ
ተነሽ ፡ ቁሚ ፡ ተዘጋጂ

ማራናታ ፣ ማራናታ
አሜን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተሎ ፡ ና
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተሎ ፡ ና
አሜን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተሎ ፡ ና
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተሎ ፡ ና (፪x)