ሚስጥርን ፡ የሚገልጽ (Misteren Yemigelts) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ሚስጥርን ፡ የሚገልጥ ፡ በሰማይ ፡ ውስጥ ፡ አለ
ዙፋኑ ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ የተከለለ
ከሰው ፡ ልብ ፡ የጠፋን ፡ ህልም ፡ ከነፍቺው
የሚያቀብል ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

ዙፋኑ ፡ በሰማይ ፡ ርቆ ፡ ከፍ ፡ ቢልም
በዓይኖቹ ፡ ከማየት ፡ ፍፁም ፡ አይታክትም
የተሰወረውን ፡ በታች ፡ በሸለቆ
እርሱ ፡ ወደ ፡ ብርሃን ፡ ይገልጠዋል ፡ አውቆ (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ከፊቱ ፡ የሚሰወር
ማነው ፡ ከእርሱ ፡ የሚደበቅ
ማነው ፡ ወጥቶ ፡ የሚገባ
ማነው ፡ አምላኬ ፡ ሳያውቅ

ያያል ፡ ያያል ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያያል
ያውቃል ፡ ያውቃል ፡ አስተውሎ ፡ ያውቃል
ዝም ፡ ቢል ፡ ቢታገስ ፡ ለፍርድ ፡ ባይቸኩል
የተወህ ፡ የረሳህ ፡ ያላየህ ፡ አይምሰልህ (፪x)

የቀድሞውን ፡ ዘመን ፡ ወይንም ፡ የአሁኑ
ገና ፡ የሚመጣውን ፡ የወደፊቱን
የፍጥረትን ፡ ሩጫ ፡ ሙሉ ፡ እንቅስቃሴ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል ፡ አምላኬ ፡ ንጉሤ (፪x)

ነገር ፡ ሁሉ ፡ ፊቱ ፡ ዕርቃኑን ፡ ይቆማል
ማን ፡ ከእርሱ ፡ ሚስጥሩን ፡ ደብቆ ፡ ያኖራል
የሰማይ ፡ የምድሩን ፡ ሁሉንም ፡ አዋቂ
ከስውርም ፡ ወጥመድ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ነጣቂ (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ከፊቱ ፡ የሚሰወር
ማነው ፡ ከእርሱ ፡ የሚደበቅ
ማነው ፡ ወጥቶ ፡ የሚገባ
ማነው ፡ አምላኬ ፡ ሳያውቅ

ያያል ፡ ያያል ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያያል
ያውቃል ፡ ያውቃል ፡ አስተውሎ ፡ ያውቃል
ዝም ፡ ቢል ፡ ቢታገስ ፡ ለፍርድ ፡ ባይቸኩል
የተወህ ፡ የረሳህ ፡ ያላየህ ፡ አይምሰልህ (፪x)