ክበር ፡ እላለሁ (Keber Elalehu) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 5:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ ነግቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ
ስላንተ ፡ ብጫወት ፡ ስላንተ ፡ ባዎጋ
እኔ ፡ አይሰለቸኝም ፡ አልታክትም ፡ ከቶ
ምላሴም ፡ አይደክም ፡ ፍቅርህን ፡ አውግቶ
አመሰግናለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ
እጅግ ፡ በገነነው ፡ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ቆሜ
በተመረጠ ፡ ቃል ፡ በሚጣፍጥ ፡ ዜማ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ መዝሙሬን ፡ ላሰማ

ክበር ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትከብር ፡ እጠግባለሁ
ንገሥ ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትነግሥ ፡ እረካለሁ

እየደጋገሙ ፡ ሥሙን ፡ ለሚያነሱ
የሚወዱትን ፡ ነው ፡ የሚያሞጋግሱ
እኔም ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ስለተያዝኩኝ
ነግቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ እጣራለሁኝ (፪x)

ጌታ ፡ እላለሁኝ
አምላኬ ፡ እላለሁኝ
ወዳጄ ፡ እላለሁኝ
ረዳቴ ፡ እላለሁኝ

አዝ፦ ነግቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ
ስላንተ ፡ ብጫወት ፡ ስላንተ ፡ ባዎጋ
እኔ ፡ አይሰለቸኝም ፡ አልታክትም ፡ ከቶ
ምላሴም ፡ አይደክም ፡ ፍቅርህን ፡ አውግቶ
አመሰግናለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ
እጅግ ፡ በገነነው ፡ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ቆሜ
በተመረጠ ፡ ቃል ፡ በሚጣፍጥ ፡ ዜማ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ መዝሙሬን ፡ ላሰማ

ክበር ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትከብር ፡ እጠግባለሁ
ንገሥ ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትነግሥ ፡ እረካለሁ

ሳይሰላቹና ፡ ፍፁም ፡ ሳይታክቱ
ክብርን ፡ ይሰጡሃል ፡ በላይ ፡ መላዕክቱ
እኔም ፡ ባለሁበት ፡ ድንኳን ፡ በጓዳዬ
ለምወድህ ፡ ጌታ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋናዬ (፪x)

ይብዛልህ ፡ ወብ ፡ አምልኮዬ
ይብዛልህ ፡ ወብ ፡ ዝማርዬ
ይብዛልህ ፡ ውብ ፡ ዕልልታዬ
ይብዛልህ ፡ ውብ ፡ ምሥጋናዬ

አዝ፦ ነግቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ
ስላንተ ፡ ብጫወት ፡ ስላንተ ፡ ባዎጋ
እኔ ፡ አይሰለቸኝም ፡ አልታክትም ፡ ከቶ
ምላሴም ፡ አይደክም ፡ ፍቅርህን ፡ አውግቶ
አመሰግናለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ
እጅግ ፡ በገነነው ፡ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ቆሜ
በተመረጠ ፡ ቃል ፡ በሚጣፍጥ ፡ ዜማ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ መዝሙሬን ፡ ላሰማ

ክበር ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትከብር ፡ እጠግባለሁ
ንገሥ ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትነግሥ ፡ እረካለሁ

ሥምህ ፡ በከንፈሬ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ ጣፍጦኛል
ባስታወስኩት ፡ ቁጥር ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አንዳንዴም ፡ ስደክም ፡ አቅም ፡ ሲከዳኝ
አምላኬን ፡ ስጠራው ፡ እበረታለሁኝ (፪x)

ጉልበቴ ፡ እላለሁኝ
ብርታቴ ፡ እላለሁኝ
ድጋፌ ፡ እላለሁኝ
ምርኩዜ ፡ እላለሁኝ

አዝ፦ ነግቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ
ስላንተ ፡ ብጫወት ፡ ስላንተ ፡ ባዎጋ
እኔ ፡ አይሰለቸኝም ፡ አልታክትም ፡ ከቶ
ምላሴም ፡ አይደክም ፡ ፍቅርህን ፡ አውግቶ
አመሰግናለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ
እጅግ ፡ በገነነው ፡ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ቆሜ
በተመረጠ ፡ ቃል ፡ በሚጣፍጥ ፡ ዜማ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ መዝሙሬን ፡ ላሰማ

ክበር ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትከብር ፡ እጠግባለሁ
ንገሥ ፡ እላለሁ (፫x) ፡ ስትነግሥ ፡ እረካለሁ