ካህኔ (Kahenie) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

በሞት ፡ ያልተሻረ ፡ በሞት ፡ ያልተገታ
በሰማይም ፡ ቀጥሏል ፡ ክህነቱ ፡ የጌታ
ሌሎቹ ፡ እንዳይኖሩ ፡ ሞት ፡ ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ፡ ክህነት ፡ የኢየሱስ ፡ ይበልጣል

ካህኔ ፡ እንደመልከፄዴቅ : ካህኔ ፡ ለዘላለም ፡ ሹም ፡ ነህ
ካህኔ ፡ ለእኔም ፡ ሕይወት ፡ መዳን : ካህኔ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ
ካህኔ ፡ በማይጠፋው ፡ ክህነት : ካህኔ ፡ በማይሽረው ፡ ሞት
ካህኔ ፡ የምትማልድልኝ : ካህኔ ፡ ቆመህ ፡ በአብ ፡ ፊት

ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ
ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x)

ካህኔ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ያለሀው : ካህኔ ፡ የነፍሴ ፡ ጠበቃ
ካህኔ ፡ መከራዬ ፡ እንዲቆም : ካህኔ ፡ ሀዘኔ ፡ እንዲያበቃ
ካህኔ ፡ የጥልን ፡ ግድግዳ : ካህኔ ፡ በሞት ፡ አፈረስህ
ካህኔ ፡ ለበደሌ ፡ መስዋዕት : ካህኔ ፡ ደምህን ፡ አፈሰስህ

በሞት ፡ ያልተሻረ ፡ በሞት ፡ ያልተገታ
በሰማይም ፡ ቀጥሏል ፡ ክህነቱ ፡ የጌታ
ሌሎቹ ፡ እንዳይኖሩ ፡ ሞት ፡ ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ፡ ክህነት ፡ የኢየሱስ ፡ ይበልጣል

የካህናት ፡ አለቃ ፡ የበጎች ፡ እረኛ
የእውነተኛዋ፡ ድንኳን : መካከለኛ
በኔ ፡ ፈንታ ፡ የሞተ ፡ የሆነልኝ ፡ ቤዛ
ነፍሴ ፡ በጣም ፡ ረክታለች ፡ ለእርሱ ፡ ስትገዛ

መድህኔ ፡ የመቀበርያዬን : መድህኔ ፡ ጉድጓድ ፡ የደፈንከው
መድህኔ ፡ የሕይወቴን ፡ ጨለማ : መድህኔ ፡ ገለል ፡ ያደረከው
መድህኔ ፡ በሞትና ፡ በእኔ : መድህኔ ፡ መካከል ፡ ገብተህ
መድህኔ ፡ ሕያው ፡ አደረከኝ : መድህኔ ፡ አንተ ፡ ተችሎህ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ
ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x)

መድህኔ ፡ ዛሬስ ፡ ብርሃን ፡ ነው : መድህኔ ፡ ቀን ፡ ሆኖ ፡ ለነፍሴ
መድህኔ ፡ ባንተ ፡ ተሰበረ : መድህኔ ፡ ለቅሶና ፡ ትካዜ
መድህኔ ፡ ፍጻሜዬ ፡ እንዲያምር : መድህኔ ፡ የመጨረሻዬ
መድህኔ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ : መድህኔ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ
ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x)