From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ውለታውን ፡ ተናግሮ ፡ ያበቃ
እግዚአብሔርን ፡ አክብሮ ፡ የረካ
ማነው ፡ እርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ያለቀበት
ያልተረዳ ፡ የዛሬውን ፡ ምህረት
ከትናንቱ ፡ በላይ ፡ እንደሆነ
በብዙ ፡ እጥፍ : ብዝቶ፡ እንደገነነ
የዛሬውን ፡ ቸርነት/ደግነት ፡ የረሳ
ለማመሥገን ፡ በፍጥነት ፡ ይነሳ (፪x)
አዝ፦ እኔስ ፡ ከትናንቱ ፡ የዛሬው ፡ ባሰበኝ
ካለፉት ፡ ዓመታት ፡ የሆነው ፡ ላቀብኝ
ፍቅር ፡ ደግነቱ ፡ ምህረቱ ፡ ገነነ
ከማስበው ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሆነ
እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ሁሌ ፡ እያሳቀኝ
አፌን ፡ በምስጋና: ምላሴን ፡ በዕልልታ ፡ እየሞላብኝ
ነፍሴን ፡ የሚያረካ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ
እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ዘወትር ፡ በየለቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታዬ ፡ አመሠግናለሁ (፭x)
ተናግሬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ተዓምሩን
ይገልጠዋል ፡ በድጋሚ: ክብሩን
በላይ ፡ በላይ ፡ እየጨማመረ
እያበዛ ፡ ደግሞ ፡ እያከበረ
በዘመናትና ፡ በዓመታቱ
ሳያጓድል ፡ ሳይሰስት ፡ ንብረቱን
ያስጉዘኛል/ያስኬደኛል ፡ በድል ፡ ሰረገላ
ምን ፡ ልበለው ፡ ከተመሥገነ ፡ ሌላ (፪x)
ምስጋናዬ የበዛበት ምክንያቴ ብዙ ብዙ ነው
የተጙዝኩበት ጎዳና ያ ዘመን ምስክሬ ነው
ካንደኛው የህይወት ምዕራፍ ወደሌላው ስሸጋገር
ብርሀኑን እያበራ የመራኝ አምላኬ ይክበር (፪x)
ማዳኑን ፡ ስላየሁ ፡ አመሠግናለሁ (፫x)
ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፫x)
ቀኖቹ ፡ ቢያወሩ ፡ ቢመሰክሩት (፫x)
አቤት ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራት (፫x)
ሥሙን ፡ እባርከዋለሁ (፫x)
ሥሙን ፡ እቀድሰዋለሁ (፫x)
ነፍሴና ፡ ሥጋዬ ፡ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አቅርቡ
አጥንቶቼም ፡ ጭምር ፡ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ አቅርቡ
የሰራላችሁን ፡ የማዳኑ ፡ ሥራ ፡ አስቡ (፪x)
አልበቃኝም ፡ አመሥግኜው (፪x) ፡ አልበቃኝም
እኔ ፡ አልረካሁም ፡ አመሥግኜው (፪x) ፡ አልረካሁም (፪x)
|