እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው (Ende Egziabhier Yale Manew) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ኦሆሆ ፡ አምላኬም ፡ ቢናገር ፡ ቢል ፡ እንደኔ ፡ ማን ፡ ነው
እውነተኛነቱን ፡ እራሱን ፡ ቢያውቀው ፡ ነው
የሚያመልኩት ፡ ሁሉ ፡ ቢሉ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ማን ፡ ነው
መልካም ፡ አገዛዙን ፡ ፅድቁን ፡ ቀምሰውት ፡ ነው

እኔ ፡ እላለሁ (፫x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ነው
እንደ ፡ አምላኬ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ነው
ማን ፡ ነው (፫x)

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና
በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና
እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ
ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x)

ቁመተ ፡ ረዥም ፡ ሰፊ ፡ ትከሻ
ለንጉሥነት ፡ አምላክ ፡ የሚሻ
መሰለውና ፡ ተንጐራደደ
እኔ ፡ ነኝ ፡ ብቁ ፡ ብሎ ፡ ፈረደ
አምላኬ ፡ መቼ ፡ ሊያይ ፡ እንደ ፡ ሰው
የፊት ፡ የፊቱን ፡ ከላይ ፡ ያለው
እርሱ ፡ ወደ ፡ ውስጥ ፡ አጥርቶ ፡ ያያል
ልበ ፡ ቀናውን ፡ መርጦ ፡ ይሾማል
ቢረሳም ፡ እንኳን ፡ በሰዎች ፡ ከቶ
በጌታ ፡ ፊት ፡ ግን ፡ ይታያል ፡ ጐልቶ
ዳዊት ፡ ትንሹ ፡ ተጠርቶ ፡ መጣ
ከታች ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ በቅባት ፡ ወጣ
ተንበሸበሽ ፡ በተስፋ ፡ ቃል
ነገ ፡ በእስራኤል ፡ ንጉሥ ፡ ሊባል
የተረሳውን ፡ የሚያይ ፡ አምላክ
ለዘለዓለም ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና
በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና
እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ
ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x)

ቢዶሉትብህ ፡ ቢመካከሩ
በጥልቅ ፡ ጉድጓድ ፡ አንተን ፡ ሊቀብሩ
ሞተሃል ፡ ብለው ፡ ቢነዙ ፡ ወሬ
በዱር ፡ ሰጠመ ፡ ተበላ ፡ በአውሬ
ሕልም ፡ አሳይቶ ፡ ተስፋ ፡ ሰጥቶሃል
ለነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ መች ፡ ይሰጥሃል
በአሕዛብ ፡ ምድር ፡ ብትሰደድም
የያዝከው ፡ ተስፋ ፡ መሆኑ ፡ አይቀርም
በግብጽ ፡ ምድር ፡ ብትሆን ፡ ግዞት
የተነገረህ ፡ ቃሉ ፡ እርሱ ፡ አይሞት
ጊዜን ፡ ጠብቆ ፡ ይከናወናል
አሳዳጆችህ ፡ ይሰግዱልሃል
ቢመስልም ፡ ነገር ፡ የተጓተተ
የሌላው ፡ ሚስጥር ፡ ሲፈታ ፡ በአንተ
በተጣልክበት ፡ አብሮ ፡ የሆነው
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና
በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና
እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ
ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x)

ሀማ ፡ ቢፎክር ፡ ቢያኖር ፡ መስቀያ
አንተ ፡ ግን ፡ ዘምር ፡ በኃሌሉያ
ሲያልፍ ፡ ሲያገድም ፡ ቁጭ ፡ በል ፡ በፊቱ
የእጁን ፡ ልትቀማው ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ
ንጉሡ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ይቀሰቀሳል
መዝገብን ፡ ይዞ ፡ ያገላብጣል
ያን ፡ ጊዜ ፡ ነገር ፡ ይለዋወጣል
ሹሙት ፡ አንግሡ ፡ ቀቡት ፡ ይባላል
አምላክህ ፡ ፃዲቅ ፡ ፈራጂ ፡ ነውና
ሳትደናገጥ ፡ ጠብቅ ፡ ቁምና
በፊትህ ፡ መውደቅ ፡ የጀመረው
ፈጽሞ ፡ ይወድቃል ፡ ድል ፡ የአንተ ፡ ነው
በአንተ ፡ ጀምሮ ፡ በአንተ ፡ ይፈጽማል
የአይሁድ ፡ መዳን ፡ ይረጋገጣል
መርደኪዮስ ፡ ሆይ ፡ አባክህ ፡ ፅና
የጌታን ፡ ክብር ፡ ልታይ ፡ ነውና

አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና
በፅድቁ ፡ ተመካ/ልመካ ፡ በእውነቱ ፡ ተጽናና/ልጽናና
እንደ ፡ ሰው ፡ አያይም ፡ አይበይንም ፡ እርሱ
ፍርዱም ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ንፁህ ፡ ነው ፡ መቅደሱ (፪x)