እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ (Elef Wede Mado) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ
አረገኝ ፡ ማዳኑን ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ
ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ
አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ
ሁሉ ፡ እንዲደነቁ

ከልምምድ ፡ ውጪ ፡ ከተዘወተረው
አዲስ ፡ ነገር ፡ መስራት ፡ ልማዱ ፡ የሆነው
በውኃ ፡ ላይ ፡ እንድሄድ ፡ እንድቆም ፡ አዘዘኝ
ቃል ላከልኝና፡ አትፍሪ ፡ ነይ ፡ አለኝ
ውኃ ፡ ላይ ፡ በታንኳ ፡ ሁሌ ፡ ከመንሳፈፍ
ኢሄም ፡ አለ ፡ ብሎ ፡ አደረገኝ ፡ እልፍ
ከታንኳ ፡ ያልወረዱ ፡ ቢሉም ፡ ምትሃት ፡ ነው
ለካስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ውኃም ፡ መንገዱ ፡ ነው

አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ
አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ
ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ
አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ
ሁሉ ፡ እንዲደነቁ

እንሂድ ፡ ወዲያማዶ ፡ እንሂድ ፡ እንሻገር
ሥሙም ፡ ጌርጌስኖን ፡ ወደሚባል ፡ አገር
ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ብዙ ፡ የተቸገረ
በመቃብር ፡ ስፍራ ፡ አለና ፡ የታሰረ
እልፍ ፡ እንበልና ፡ የታሰረ ፡ ይፈታል
ብሎ ፡ ሲያሻግረን ፡ ይሄ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ
በስፍራው ፡ ስንደርስ ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ ተፈወሰ
ጌታም ፡ ተገናኘው ፡ ልቡም፡ ተመለሰ

አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ
አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ
ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ
አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ
ሁሉ ፡ እንዲደነቁ

ሌሊቱን ፡ በሙሉ ፡ ስደክም ፡ ፍለጋ
መረቤም ፡ አንድ ፡ ዓሣ ፡ ሳይዝልኝ ፡ ነጋ
የጌታን ፡ ቃል ፡ ይዤ ፡ ስጥል ፡ ወደ ፡ ጥልቁ
ታንኳዬን ፡ ዓሣዎች ፡ ሞልተው ፡ አስጨነቁ
መሄድ ፡ እንደቃሉ ፡ ፈቀቅ ፡ ማለት
በውስጡ ፡ አለና ፡ ብዙ ፡ በረከት
ገፍቶ ፡ አስጠግቶኝ ፡ አድርጐኝ ፡ እልፍ
በመንፈሱ ፡ ሙላት ፡ ሆነ ፡ መንሳፈፍ

አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ
አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ
ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ
ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ
አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ
ሁሉ ፡ እንዲደነቁ