From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንደ ፡ ጀግና ፡ ወንድ/ሰው ፡ እንደ ፡ እልፍ ፡ ገዳይ
እንጐራደዳለሁ/ፎክርበታለሁ ፡ በጠላቴ ፡ ላይ
ተረታው ፡ ሳይል ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ
ማጥቃት ፡ መዋጋትን ፡ አልተውም ፡ ከቶ (፪x)
ተወርውሮ ፡ ከቶ ፡ የማይስተው
የጌታዬ ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ነው
ደጋግሜ ፡ እርሱን ፡ ጠራዋለሁ
በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ እላለሁ
ሲቀረቀር ፡ በግንባሩ ፡ ላይ
በእጄ ፡ ያለው ፡ የያዝኩት ፡ ድንጋይ
ላዩ ፡ ቆሜ ፡ አንገቱን ፡ ቆርጥና
አውጃለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ዝና
አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ
አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x)
እኔም ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰው
በሕዝቤ ፡ ጠላት ፡ ላይ ፡ ሥምህን ፡ ላንሳው
በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ልግባ
ጠላትን ፡ ዘርሬ ፡ ላፍስስ ፡ የደስታ ፡ እንባ
እኔ ፡ እያየሁ ፡ ጐልያድ ፡ በእስራኤል ፡ ላይ ፡ አይፎክርም
እኔ ፡ እያለሁ ፡ ጠላት ፡ በሕዝቤ/በምድሬ ፡ ላይ ፡ አይዘብትም (፪x)
የአንበሳን ፡ ደቦል ፡ የሚገነጥል
ግዙፉን ፡ ሠራዊት ፡ ሰባብሮ ፡ የሚጥል
የአምላኬ ፡ ክብሩ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከቶ ፡ እንደምን ፡ ልስጋ ፡ እንዴትስ ፡ ልፍራ (፪x)
ፍልስጤሞች ፡ ያገኙኝ ፡ መስሏቸው
በመንደሩ ፡ ሞላ ፡ ዕልልታቸው
በጠንካራዉ ፡ ገመድ ፡ አስረውኛለው
በእነሱ ፡ ቤት ፡ ማን ፡ ያስጥለኛል
ወረደብኝ ፡ መንፈሱ ፡ የጌታ
እስራቴም ፡ ላላ ፡ ተፈታታ
በእጄ ፡ ገቡ ፡ ጠፉ ፡ ጠላቶቼ
ገመድኳቸው ፡ መጥቼ ፡ ፈትቼ
አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ
አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x)
አሞት ፡ ይሆናል ፡ ወይ ፡ መንገድ ፡ ሄዶ
አንቀላፍቶም ፡ ይሁን ፡ ይህ ፡ ከንቱ ፡ ባዶ
በአሕዛብ ፡ አምላክ ፡ እሳለቃለሁ
በማንነቱም ፡ ላይ ፡ እዘብታለሁ (፪x)
አምላክ ፡ ሳይሆን ፡ አምላክ ፡ ነኝ ፡ ባዩን
መዘዝኩበት ፡ ስለታም ፡ ሰይፌን
ነብያቱን ፡ በሙሉ ፡ አረድኳቸው
እስቲ ፡ ያድን ፡ ይምጣ ፡ አምላካቸው
የሚመልስ ፡ በእሳት ፡ ተገልጦ
የአሕዛብን ፡ አምላክ ፡ አስደንግጦ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር
ከፍ ፡ ብሎ ፡ ተከብሮ ፡ የሚኖር
አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ
አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ኤልያስ
በምድር ፡ ኢትዮጵያ ፡ ላይ ፡ ሥምህ ፡ እንዲነግስ
ከበአል ፡ ነቢያት ፡ እወራረዳለሁ
ክብርህን ፡ ስትገልጥ ፡ እረታቸዋለሁ
እኔ ፡ እያየሁ ፡ በአል ፡ አምላክ ፡ ተብሎ ፡ አይመለክም
እኔ ፡ እያለሁ ፡ የጌታዬ/የኢየሱስ ፡ ክብር ፡ አይሸፈንም (፪x)
አንተ ፡ እያለህ ፡ እውነት ፡ እንጂ ፡ ውሸት ፡ አይሰበክም
አንተ ፡ እያለህ ፡ ወንጌል ፡ እንጂ ፡ ክደት ፡ አይነገርም
አንቺ ፡ እያለሽ ፡ እውነት ፡ እንጂ ፡ ውሸት ፡ አይሰበክም
አንቺ ፡ እያለሽ ፡ ወንጌል ፡ እንጂ ፡ ክደት ፡ አይነገርም
|