የንጉሥ ፡ ቤተሰብ (Yenegus Bieteseb) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አገኘሁ ፡ መላ ፡ ያለበት ፡ ቤት
አገኘሁ ፡ ፍርድ ፡ የሚሰጥበት
ለዚህ ፡ ነው ፡ የተረጋጋሁት (፪x)

ልዑል ፡ ነው ፡ ልዑል ፡ ነው ፡ አባቴ (፪x)
ዝማሬው ፡ ይፈልቃል ፡ ከቤቴ

እንዴት ፡ ይመኛል ፡ ልቤማ ፡ ሌላ
ተስተናግጄ ፡ ከንጉሥ ፡ ጋራ
ተቆረሰና ፡ የሰላም ፡ ማዕድ
ቤቱ ፡ ይሞቃል ፡ አያስገባም ፡ ብርድ

አሃ ፡ አሃ ፡ ለተጨነቀማ ፡ ግራ ፡ ለገባዉ
ትክክለኛው ፡ መልስ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ ያለው (፪x)

ተራራው ፡ ተጋርዶ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ሳየው
ጌታ ፡ እንዳስለመደኝ ፡ እጄን ፡ አነሳሁ
በመንፈስ ፡ የሆንን ፡ አምልኮን ፡ ስሰዋ
የት ፡ እንደ ፡ ሄደ ፡ አላውቅም ፡ ወዴት ፡ እንደገባ

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጠራኛ/የቀባኛ (፪x)

ሊነካኝ ፡ አይችልም ፡ ጠላቴ (፪x)
እሳቱ ፡ ከቦኛል ፡ የአባቴ
አትንኩት ፡ አትንኩት ፡ ይላሉ (፪x)
ይታያል ፡ ደሙ ፡ በጉበኑ
አትንኳት ፡ አትንኳት ፡ ይላሉ
አትንኩት ፡ አትንኩት ፡ ይላሉ
ይታያል ፡ ደሙ ፡ በጉበኑ

ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ ቢታሰር ፡ እጃቸው
አምልኮ ፡ አላቆሙም ፡ ተፈቷል ፡ ውስጣቸው
ሊጠፋ ፡ አይችልም ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ እሳት
እንደውም ፡ ይብሳል ፡ ሲቆሰቁስት

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የቀባኛ/የጠራኛ (፪x)

ወዴት ፡ ወዴት ፡ ወዴት (፪x)
እንዴት ፡ እንዴት ፡ ይመኛል
እንዴት ፡ እንዴት ፡ እንዴት

የንጉሥ ፡ ቤተሰብ ፡ አይመኝም ፡ ሌላ
አምሮበት ፡ ይኖራል ፡ ከእጁ ፡ እየበላ
የንጉሥ ፡ ቤተሰብ ፡ አይመኝም ፡ ውጪ
ያበድራል ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ ተረጂ

የእኔ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ለዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጠራኛ/የቀባኛ (፪x)