ይደክመኛል ፡ መኖር (Yedekmegnal Menor) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ ፡ የማይተኛ (፪x)
የሕይወቴ ፡ ጠበቃ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እንዳልሰጋ (፪x)

እኔማ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ
አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ
ዓለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ
አይወድቅም ፡ በንፋስ ፡ ቤቴ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ተዋድጄ
ይፈልቃል ፡ ሰላም ፡ ከደጄ

ለካ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x)
የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው (፪x)

ኧረ ፡ እኔ
አመል ፡ ሆኖብኛል ፡ አመል (፪x)
ስነሳ ፡ ስቀመጥ ፡ ለክብርህ ፡ መዘመር
እንደዚህ ፡ ካልሆነ ፡ ይደክመኛል ፡ መኖር

የእኔ ፡ ነህ (፪x)
የእኔ ፡ ነህ ፡ ብልህ
ከመሞት/ከጭንቀት ፡ ያዳንከኝ
ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x)

ከእንግዲህማ ፡ ወዳጅ ፡ አግኝቻለሁ
ከእንግዲህማ ፡ አብሮ ፡ የሚዘልቅ
ከእንግዲህማ ፡ እንዲህ ፡ ከወደደ
ከእንግዲህማ ፡ ጥሎ ፡ የማይሄድ (፪x)

የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ ፡ የማይተኛ (፪x)
የሕይወቴ ፡ ጠበቃ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እንዳልሰጋ (፪x)

እኔማ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ
አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ
ዓለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ
አይወድቅም ፡ በንፋስ ፡ ቤቴ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ተዋድጄ
ይፈልቃል ፡ ሰላም ፡ ከደጄ

ለካ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x)
የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው (፪x)