ጠራኝ (Teragn) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ቦታዬ ፡ አይደለም ፡ የክትከታው ፡ ሥር
ሕዝብ ፡ ይጠብቀኛል ፡ እንዳገለግል
ውሰደኝ ፡ አልልም ፡ አበቃልኝ
የኪዳን ፡ ሰው ፡ ነኝ ፡ አሃ ፡ ጥሪ ፡ አለብኝ

ሲያስፈራራኝ (፫x) ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስፈራራኝ
እግዚአብሔር ፡ ቀደመና ፡ ቅስሙን ፡ ሰበረው
መታልኝ ፡ መለሰልኝ
ሲያስፈራራኝ (፫x) ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስፈራራኝ
እግዚአብሔር ፡ ቀደመና ፡ ቅስሙን ፡ ሰበረው
መታልኝ ፡ ተው ፡ አለልኝ ፡ (ተው ፡ አለልኝ)

ጠራኝ ፡ በቁልምጫ ፡ ሥም ፡ (ጠራኝ)
ጠራኝ ፡ እያሞካሸ ፡ (ጠራኝ)
ጠራኝ ፡ ከዛኛው ፡ ዓለም ፡ (ጠራኝ)
ጠራኝ ፡ ሊሰጠኝ ፡ ሰላም ፡ (ጠራኝ)

ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ጌታዬ/ከአንገቴ ፡ ቀና
መቼ ፡ ጨረስኩኝ ፡ ገና ፡ ነው ፡ ገና (፪x)

የት ፡ አገኘው ፡ ነበር ፡ ይህንን ፡ ሰላም
አምልከው ፡ ይለኛል ፡ አያሰኝም ፡ ዝም
የት ፡ አገኘው ፡ ነበር ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ደስታ
በዚህ ፡ ከቦዘን ፡ አይኖርልኝ ፡ ጌታ

ሲያስፈራራኝ (፫x) ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስፈራራኝ
እግዚአብሔር ፡ ቀደመና ፡ ቅስሙን ፡ ሰበረው
መታልኝ ፡ መለሰልኝ
ሲያስፈራራኝ (፫x) ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስፈራራኝ
እግዚአብሔር ፡ ቀደመና ፡ ቅስሙን ፡ ሰበረው
መታልኝ ፡ ተው ፡ አለልኝ ፡ (ተው ፡ አለልኝ)