ጌታ ፡ አለኝ (Gieta Alegn) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አምላኬ ፡ ነው ፡ የደገፈኝ ፡ እንዳልወድቅ ፡ በድካሜ
በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ ሆኖ ፡ ሳይለየኝ ፡ ከአጠገቤ
ከኋላዬ ፡ ሲከተለኝ ፡ እንቅፋቱ ፡ እንዳይጐዳኝ
የጠላዬን ፡ ወጥመድ ፡ ሰብሮ ፡ መኖሪያዬ ፡ ሆነልኝ

አሃ ፡ ሲከተለኝ
አሃ ፡ ከኋላዬ
አሃ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው
አሃ ፡ ከለላዬ
አሃ ፡ ቀኑ ፡ ሲከፋ
አሃ ፡ ሲጨልም
አሃ ፡ ወንድም ፡ አለኝ
አሃ ፡ አይዞህ ፡ የሚል

ጌታ ፡ አለኝ (፲፪x)

ቅጥር ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ ያለፍኩት
አላልፈው ፡ ነበር ፡ ባይኖረኝ ፡ አባት
የትላንቱ ፡ ያን ፡ ጨለማ
ይገርመኛል ፡ ኧረ ፡ እንዴት (፪x) ፡ እንዴት ፡ ጠፋ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ የነደደው
እሳት ፡ ጠፍቷል ፡ ጌታዬን (፪x) ፡ ላመስግነው

ዋስትናዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x)
ከለላዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x)

የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስበው
የዛሬን ፡ ቀን ፡ ስላየልኝ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው ፡ ጌታ ፡ ነው
ለነገማ ፡ ዋስትና ፡ አለኝ ፡ ንፋስ ፡ ቢነፍስብኝ ፡ እላዬ
ከእንግዲህማ ፡ ልቤ ፡ አይፈራም ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ በታንኳዬ

አሃ ፡ ሲከተለኝ
አሃ ፡ ከኋላዬ
አሃ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው
አሃ ፡ ከለላዬ
አሃ ፡ ቀኑ ፡ ሲከፋ
አሃ ፡ ሲጨልም
አሃ ፡ ወንድም ፡ አለኝ
አሃ ፡ አይዞህ ፡ የሚል

ጌታ ፡ አለኝ (፲፪x)

ቅጥር ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ ያለፍኩት
አላልፈው ፡ ነበር ፡ ባይኖረኝ ፡ አባት
የትላንቱ ፡ ያን ፡ ጨለማ
ይገርመኛል ፡ ኧረ ፡ እንዴት (፪x) ፡ እንዴት ፡ ጠፋ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ የነደደው
እሳት ፡ ጠፍቷል ፡ ጌታዬን (፪x) ፡ ላመስግነው

ዋስትናዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x)
ቤተኛዬ ፡ ሆኗል ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)