ፍቅር ፡ አሳየኸኝ (Feqer Asayehegn) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ባላጣኸው ፡ ቦታ ፡ ባላጣኸው ፡ ልብ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ ፡ ገረመኝ ፡ ሳስብህ (፪x)

ማነው ፡ የወደደኝ ፡ ጠጋ ፡ ያረገኝ
ከመሞት ፡ አውጥቶ ፡ ፍቅር ፡ ያሳየኝ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ

የእኔማ ፡ ነገር ፡ የእኔስ ፡ ጉዳይ
ተፈጸመልኝ ፡ ጐልጐታ ፡ ላይ (፬x)

ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ
ወዶኛል ፡ ያለ፡ ልክ (፪x)

አንዴ ፡ ብቻ ፡ አይደለም
ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ ጉልበት ፡ የሆንከኝ
እምነቴ ፡ ሲላላ ፡ ከጐኔ ፡ ቆመህ ፡ ያበረታኸኝ (፪x)

ወደድከኝ (፫x)
ይቅር አልከኝ(፫x)

መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ ቢሆን
አልረሳውም ፡ የአንተን ፡ ፍቅርህን
ሰው ፡ ያረከኝ ፡ ያወጣኸኝ
ከጨለማው ፡ ከሞት ፡ ገደል (፪x)

ማነው ፡ የወደደኝ ፡ ጠጋ ፡ ያደረገኝ
ከመሞት ፡ አውጥቶ ፡ ፍቅር ፡ ያሳየኝ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ