እውነተኛ ፡ ወዳጅ (Ewnetegna Wedaj) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ከመፈጠሬ ፡ ከመታሰቤ ፡ ጀምሮ
የማትለወጥ ፡ የማትቀየር
ወረት ፡ የሌለበት ፡ አንተን ፡ ነው ፡ ያየሁት (፪x)

አዝ፦ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
እውነተኛ ፡ አፍቃሪ (፪x)
የእኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አንተ ፡ ነህ
ጊዜ/ዘመን ፡ የማይለውጥህ (፪x)

ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል
ለካስ ፡ አለው ፡ መጨረሻ
ለካስ ፡ እኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ማሸሻ

የሰው ፡ ልጅ ፡ ሆኖ ፡ የሰው
እየተባለ ፡ ማነው
ከሰማይ ፡ መጣ ፡ ከላይ
አላስችል ፡ ብሎት ፡ ሲያይ

ከሞት ፡ አወጣኝ ፡ ከሞት
ደርሶልኝ ፡ ካለሁበት
ተናገር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ሲሉኝ
ለዚህ ፡ ነው ፡ ቃላት ፡ ያጠረኝ

ሰማይ ፡ ይናገር ፡ ምድርም
ስላንተ ፡ ላውራ ፡ ዘለዓለም (፪x)

አዝ፦ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
እውነተኛ ፡ አፍቃሪ (፪x)
የእኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አንተ ፡ ነህ
ጊዜ/ዘመን ፡ የማይለውጥህ (፪x)

ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል
ለካስ ፡ አለው ፡ መጨረሻ
ለካስ ፡ እኔስ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
በቃ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ማሸሻ