የተስፋ ፡ ቃል (Yetesfa Qal) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 6.jpg


(6)

ወደፊት
(Wedefit)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

የተስፋ ፡ ቃል ፡ ሰጠኝ ፡ ገና ፡ በልጅነት ፡ እኔ ፡ አለሁ ፡ አለኝ
ሃሩሩ ፡ እንዳይጐዳኝ ፡ እባቡ ፡ እንዳይነድፈኝ ፡ እንዳይጠጋኝ
አቤት ፡ የተነሳው ፡ የጠላት ፡ ዘመቻ ፡ ገፍቶ ፡ ሊጥለኝ
የእርሱ ፡ ቤት ፡ ደካማ ፡ የእኔ ፡ ግን ፡ በጌታ ፡ ሄደ ፡ እየበረታ

የእኔ ፡ ዳኛ ፡ ከጐኔ ፡ ነበር (፪x) ፡ ከጐኔ (ከጐኔ ፡ ከጐኔ)
የእኔ ፡ ዳኛ ፡ ከጐኔ ፡ ነበር (፪x) ፡ ከጐኔ (ከጐኔ ፡ ከጐኔ)
የእኔ ፡ ዳኛ ፡ ከጐኔ ፡ ነበር (፪x) ፡ ከጐኔ (ከጐኔ ፡ ከጐኔ)

ገና (፫x) ፡ ገና ፡ ነው
ገና (፫x) ፡ ነው

ገና ፡ ነው ፡ የአባቴ ፡ ስራ
ገና ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የጀመረው
ገና ፡ ነው ፡ መቼ ፡ ተፈጸመ
ገና ፡ ነው ፡ ማነው ፡ ቆሟል ፡ ያለ (፪x)

በእጄ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ በትር ፡ ከሆነማ ፡ ባሕሩን ፡ ምታው
ለአንተ ፡ መንገድ ፡ አለ ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አብ ፡ ያዘጋጀው
ዛሬ ፡ የከበደህ ፡ ያስደነገጠኽን ፡ የግብጹን ፡ ጦረኛ
በመዝሙር ፡ ልጣለው ፡ ጆሮዎችህን ፡ ስጠኝ ፡ ና ፡ ተባበረኛ

(አሃሃሃሃሃ) መንፈሱ ፡ በላዬ ፡ አሁን ፡ መጣብኝ
(አሃሃሃሃሃ) ያለህበት ፡ ችግር ፡ ግልጽ ፡ ሆኖ ፡ ታየኝ
(አሃሃሃሃሃ) ለዚህማ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና ፡ ነው ፡ መልሱ
(አሃሃሃሃሃ) አሁን ፡ ተነሳልህ ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉሡ

ወደቀልህ ፡ ሰንሰለቱ ፡ በኢየሱስ ፡ በክንደ ፡ ብርቱ
ወደቀልህ ፡ በሽታው ፡ ለዘላለም ፡ እንዳታየዉ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል
እንዲህ ፡ ይለኛል ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል (፪x)

ገና (፫x) ፡ ገና ፡ ነው
ገና (፫x) ፡ ነው

ገና ፡ ነው ፡ የአባቴ ፡ ስራ
ገና ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የጀመረው
ገና ፡ ነው ፡ መቼ ፡ ተፈጸመ
ገና ፡ ነው ፡ ማነው ፡ ቆሟል ፡ ያለ (፪x)