ፅላት (Tselat) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 6.jpg


(6)

ወደፊት
(Wedefit)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2015)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ኦሆ ፡ የምትቀርበኝ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ኦሆ ፡ የምጠብቀኝ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ ኦሆ ፡ የቆዘምኩ ፡ ለታ
ፍቅርህ ፡ ይሰማኛል ፡ ኦሆ ፡ አልፏ ፡ የእኔን ፡ ሁኔታ
     
     በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ
     ይቀሰቅሰኛል ፡ ሀሌሉያ ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ
     በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ
     ይቀሰቅሰኛል ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ

ኦሆሆሆሆሆ ፡ ላምልክ (፰x)

አይደክመኝም ፡ በቃ ፡ አምልኬ ፡ አምልኬ ፡ ልብህ ፡ እስኪረካ
የኔንም ፡ መስዋእት ፡ የፃፍኩትን ፡ መዝሙር ፡ ወደኀዋል ፡ ለካ
የቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ በፊትህ
አንተን ፡ እያመለኩኝ ፡ እያከበርኩህ

እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላምልክ (፪x)
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላምልክህ
ውለታህን ፡ ሳስበው ፡ መግለጫ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ ፡ አዎ
ያንትን ፡ ፍቅር ፡ ሳስብ ፡ መግለጫ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ ፡ አዎ

በጨለማው ፡ ሀገር ፡ ኦሆ ፡ ሀጥያት ፡ ክብዶብኝ
ማነው ፡ ከዚህ ፡ ስቃይ ፡ ኦሆ ፡ የሚያሳርፈኝ
በሞት ፡ ተከብቤ ፡ ኦሆ ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ሳለ
በፍቅርህ ፡ አድነህ ፡ ኦሆ ፡ ታሪኬን ፡ ለወጥከው

     በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ
     ይቀሰቅሰኛል ፡ ሀሌሉያ ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ
     በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ
     ይቀሰቅሰኛል ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ

ኦሆሆሆሆሆ ፡ ላምልክ (፰x)