የሕይወቴ ፡ እረኛ (Yehiwotie Eregna) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

እኮ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ መሪ ፡ ነህ
አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ነህ
ልቤን ፡ ለአንተ ፡ ትቼዋለሁ
ዘለዓለም ፡ አምልክሃለሁ (፫x)

እውነትን ፡ ልናገር ፡ አይዋሽ ፡ አንደበቴ
ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ አባቴ
ሁሉንም ፡ አስናቀኝ ፡ እኔም ፡ ሁሉን ፡ ተውኩት
ጌታዬ ፡ እንደሚሻል ፡ ውስጤን ፡ አሳመንኩት

አዝ፦ አለኝ ፡ ልበል
እኔ ፡ አለኝ ፡ ልበል
አለኝ ፡ ልበል ፡ አባት
ውስጤ ፡ ያረፈበት/የኮራበት (፪x)

ከሲና ፡ መጣ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክብር
ሕግን ፡ ሊያወጣ ፡ ለዚች ፡ ለምድር
በእራሱ ፡ ፈቃድ ፡ የሚጓዘውን ፡ ሕዝብ
በእግዚአብሔር ፡ ፀጋ ፡ እንዲተዳደር
ካለፈው ፡ ኪዳን ፡ የሚሻል ፡ ኪዳን
የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ መጣ
በሰው ፡ ጫንቃ ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው ፡ ቀንበር ፡ ተፈታ

አዝ፦ አለኝ ፡ ልበል
እኮ ፡ አለኝ ፡ ልበል
አለኝ ፡ ልበል ፡ አባት
ውስጤ ፡ ያረፈበት (፪x)

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው
የሚያሳጣኝም ፡ የለም ።
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳድረኛል
በእረፍቱ ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ይመራኛል ።
ነፍሴን ፡ መለሳት
ስለ ፡ ሥሙም ፡ በፀድቅ ፡ መንገድ ፡ መራኝ ። [1]

  1. መዝሙር ፡ ፳፫ ፡ ፩ - ፫ (Psalm 23:1-3)