የግሌ ፡ ነህ (Yegelie Neh) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ
አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ
የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ
ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ

ለታላቅነትህ ፡ ሲወራ ፡ ሲተረክ
ቃላቶች ፡ አቅም ፡ አጠራቸው ፡ ለመግለጽ
ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
ከምድርም ፡ በታች ፡ በታች ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
እንደ ፡ ገለፅክልን ፡ ሥምህን ፡ ልባርክህ (፪x)

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ
አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ
የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ
ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ

አትታማም ፡ ክፉ ፡ አድርገሃል ፡ ተብለህ
ለልጆችህ ፡ ሁሌ ፡ መልካም ፡ ነህ
ከማደሪያህ ፡ ቃል ፡ ትልካለህ
የዛለን ፡ ልብ ፡ ታሳርፋለህ

አምላክ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x)
ንጉሥ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x)
ኃያል ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፫x)

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ
አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ
የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ
ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ