ሃሩሩ ፡ በረደ (Haruru Berede) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:20
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ሃሩሩ ፡ በረደ ፡ ጥላ ፡ በዝቶ
ከጥሜም ፡ እረካሁ ፡ ውኃ ፡ ፈልቆ
በቃ ፡ ሲል ፡ አበቃ ፡ መጨነቄ
አሻገርከኝ ፡ ያንን ፡ ዘመን ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x)

ሁልጊዜ ፡ ይነገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር
ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ
ያለፈ ፡ ይናገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር
ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ

አልተለየኸኝም ፡ በጭንቀቴ
ደግፈህ ፡ አቆምከኝ ፡ መድኃኒቴ
አጸናኸው ፡ እግሬን ፡ እንደ ፡ ዋላ ፡ እግር
ከልቤ ፡ ልበልህ ፡ ተመሥገን

አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x)

ሳስበው ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ዞር ፡ ብዬ
ከችግር ፡ የተነሳ ፡ ተጨንቄ
ማን ፡ ያሳልፈኛል ፡ ያልኩትን
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ያሳለፍከኝ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ
ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ
ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x)

ሁልጊዜ ፡ ይነገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር
ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ
ያለፈ ፡ ይናገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር
ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ (፪x)