ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው (Gietayie Eko New) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ከወደቅኩበት ፡ ያነሳኝ (፪x)

ያነሳኝ ፡ ያነሳኝ ፡ ያነሳኝ

አዝ፦ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፡ ፊት ፡ ያቆመኝ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው (፫x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ መድኃኒቴ ፡ ኢየሱስ
ከክፉ ፡ ያዳንኸኝ ፡ የጋረድከኝ ፡ ኢየሱስ
ለዛሬም ፡ አልፈራም ፡ አንተን ፡ ታምኛለሁ
ለነገም ፡ አልፈራም ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ይዤአለው (፪x)

አዝ፦ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፡ ፊት ፡ ያቆመኝ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው (፫x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ መድኃኒቴ ፡ ኢየሱስ
ከክፉ ፡ ያዳንኸኝ ፡ የጋረድከኝ ፡ ኢየሱስ
የሚጠብቀኝን ፡ የሞት ፡ ፅዋ ፡ ደፍተህ
እንዳይብረከረክ ፡ ጉልበቴን ፡ አፅንተህ
ዓለት ፡ ላይ ፡ እንደ ፡ ቆመው ፡ እንዳማረው ፡ ቤትህ
ሕይወቴ ፡ ተዋበ ፡ አንተ ፡ የገባህ ፡ ለት

አዝ፦ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፡ ፊት ፡ ያቆመኝ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው (፫x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ መድኃኒቴ ፡ ኢየሱስ
ከክፉ ፡ ያዳንኸኝ ፡ የጋረድከኝ ፡ ኢየሱስ
አጋር ፡ ሆነኸኛል ፡ ከፉ ፡ እንዳይነካኝ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠነከክልኝ
የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ሥሙ ፡ ያስጠልላል
አንተን ፡ የታመነ ፡ መች ፡ ክፉ ፡ ያገኘዋል

ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያረገኝ
ከወደቅኩበት ፡ ያነሳኝ (፪x)

ያነሳኝ ፡ ያነሳኝ ፡ ያነሳኝ

አዝ፦ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው (፫x)
በሰው ፡ ፊት ፡ ያቆመኝ ፡ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው (፫x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ እረኛ
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪x)