ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም (Degmo Qenu Sichelm) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ጠዋት ፡ ስነሳ ፡ ደስታ ፡ ይሆናል
የትላንትናው ፡ ሃዘን ፡ ይርቃል
እህል ፡ ባልበላም ፡ ፊትህ ፡ ያጠግበኛል
ፀጋህ ፡ ከክፉ ፡ ይጋርደኛል
ምህረትህ ፡ ከፊት ፡ ከኋላ ፡ ከቦኝ
አቤት ፡ ይገርማል ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩት

አዝ፦ ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም
ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲነጋ
ደግሞ ፡ እርጥቡ ፡ ሲደርቅ
ደግሞ ፡ ሁኔታ ፡ ሲርቅ
አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል

አምላክ ፡ ሲረዳኝ ፡ አታዩም ፡ ዎይ
ክረምቱ ፡ አልፎ ፡ በጋው ፡ ሲታይ
ከዓለቱ ፡ ልውጣ ፡ ድምጼን ፡ ላሰማ
ጌታ ፡ እንደ ፡ ረዳኝ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይስማ
ያገለገልኩት ፡ ለሥሙ ፡ የለየኝ
ቀን ፡ ቆጠረና ፡ ዋጋ ፡ ከፈለኝ

አዝ፦ ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም
ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲነጋ
ደግሞ ፡ እርጥቡ ፡ ሲደርቅ
ደግሞ ፡ ሁኔታ ፡ ሲርቅ
አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል
አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል