አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ (Amlak Yalew Yemta) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x)
እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ትልቅ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ መታሁት ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ ፈራሁት
በበረሃ ፡ ውስጥ ፡ አስተምሮኛል ፡ ኑሮ ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)
የተደበቀው ፡ ፀጋ ፡ ሲወጣ ፡ ከኮሮጆዬ
መውደቁን ፡ አውቆ ፡ ፈርቶ ፡ ሸሽቶኛል ፡ ባለ ፡ ጋራዬ (፪x)

አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x)
እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x)

የተዘጋው ፡ ከፈተውና ፡ ከፊት ፡ ከፊቴ
መሸነፍ ፡ ሳይሆን ፡ ያጋጥመኛል ፡ ድል ፡ በሕይወቴ (፪x)
የተዘራውን ፡ በቅሎ ፡ አየሁት ፡ አልጨነገፈም
በድርቁ ፡ ወራት ፡ የሌላው ፡ ሲደርቅ ፡ የእኔ ፡ አልደረቀም (፪x)

አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x)
እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ
በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ልቤ ፡ መደነቅ ፡ ተሞላ
በአንዱ ፡ ስገረም ፡ ሌላው ፡ እዚህ ፡ ደግሞ
ተዓምር ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ
ድንቅ ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ
ልዩ ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ (፪x)