አልመዝንህም (Almezenehem) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ይህንን ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ያልኩት
ጨለማውን ፡ አይቶ ፡ ልቡ ፡ የማይደነግጥ (፪x)
የችሎቱ ፡ ብዛት ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል
ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ና ፡ እንጂ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ አትፍራ ፡ ይለኛል (፪x)
አትፍራ ፡ ይለኛል

አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም
እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም
ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል
ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x)

አልመዝንህም ፡ ስለሆነና ፡ ስላልሆነ
እምነቴ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው ፡ መች ፡ ቀዘቀዘ
አያሳልፍም ፡ እኔስ ፡ አልልም ፡ ውኃውን ፡ አይቼ
ቀጥ ፡ ያለ ፡ መንገድ ፡ ይሆናል ፡ ስላለ ፡ ጐኔ

አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም
እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም
ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል
ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x)

በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ይሄ ፡ ኢየሱስ ፡ መቼ ፡ ደክሞ ፡ ያውቃል
ግራ ፡ አይገባው ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ የት ፡ ይሸበራል
ብቻ ፡ ከፊቴ ፡ ችግር ፡ ሲጋረጥ ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል
መፍትሄ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተሻገር ፡ እንጂ ፡ እረፍ ፡ ይለኛል

አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም
እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም
ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል
ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x)

ደመናን ፡ አይቶ ፡ ትንቢት ፡ መናገር ፡ ሁሉም ፡ ይችላል
ንፋሱ ፡ ሲነፍስ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይዘንባል ፡ ይላል
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ ለየት ፡ ያለው ፡ ነው ፡ ትንቢት ፡ ሲናገር
ውኃን ፡ ያመጣል ፡ እንዲሁ ፡ ደመና ፡ ሳይኖር

አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም
እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም
ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል
ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት
ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x)