አልገፋ ፡ ያለውን ፡ ቀን (Alegefa Yalewen Qen) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ተነስቷል
(Tenestual)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን
ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ
ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ
መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ

ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ
ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x)

ከኋላዬ ፡ ርቆ ፡ እንደ ፡ ህልም ፡ አለፈ
እንደ ፡ ፈሳሽ ፡ ውኃ ፡ መጨነቄ ፡ ሄደ (፪x)
ምሥጋናዬ ፡ አርጐ ፡ መቅደስህን ፡ ይሙላው
ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ ይሄም ፡ ሲያንስብህ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን
ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ
ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ
መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ

ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ
ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x)

እጅህ ፡ እየረዳኝ ፡ ሁሉን ፡ ተሻገርኩ
አልገፋ ፡ ያለውን ፡ ቀኖቼን ፡ አለፍኩ (፪x)
ለአደረከው ፡ ሥራ ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል
ነፍስ ፡ ያለው ፡ ግዑዙ ፡ ወድቆ ፡ ይሰግድልሃል (፪x)

አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን
ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ
ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ
መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ

ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ
ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ
ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x)

ምን ፡ ቢሰጥህ ፡ ምላሽ ፡ የአንተን ፡ ሥራ ፡ ይተካል
እንዲያው ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ ማመስገን ፡ ይሻላል (፪x)
እስከ ፡ ምድር ፡ ዳርቻ ፡ የሚመስልህ ፡ ታጥቷል
ትልቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ይገባሃል (፪x)

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ባለ ፡ ውለታ (፪x)

ላብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ላብዛልህ
ላብዛልህ ፡ ስግደትም ፡ ላብዛልህ (፪x)

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ባለ ፡ ውለታ (፪x)

ላብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ላብዛልህ
ላብዛልህ ፡ ስግደትም ፡ ላብዛልህ (፪x)