ተናግሬ ፡ ነበር (Tenagerie Neber) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አዝ፦ ተናግሬ ፡ ነበር ፡ አስቀድሜ ፡ እኔማ
ድሉ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ ስል ፡ ጠላቴም ፡ አልሰማ
እኔ ፡ አልመለስም ፡ ደጁ ፡ ጋር ፡ ደርሼ
ድርሻዬን ፡ እወስዳለሁ ፡ ምድሪቷን ፡ ወርሼ

ምነው ፡ ተከተለኝ ፡ ጠላቴ ፡ ከኋላ (፫x)
ተው ፡ አትከተለው ፡ ሃይ ፡ የሚለው ፡ ጠፋ (፫x)
ቃል ፡ ይዤ ፡ መውጣቴን ፡ ዘንግቶት ፡ ነበረ (፫x)
እኔ ፡ ተሻገርኩኝ ፡ እርሱ ፡ ሰምጦ ፡ ቀረ (፫x)

ፋንታዬ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማለት ፡ ለኔ
አሃ ፡ ለኔ ፡ አሃሃ ፡ ለኔ (፪x)

ደመናዉ ፡ ከላዬ ፡ ላይ
ገለል ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ፡ ይሄው ፡ ዛሬ
ይሄው ፡ ዛሬ ፡ በድሉ ፡ ጐዳና (፪x)

አዝ፦ ተናግሬ ፡ ነበር ፡ አስቀድሜ ፡ እኔማ
ድሉ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ ስል ፡ ጠላቴም ፡ አልሰማ
እኔ ፡ አልመለስም ፡ ደጁ ፡ ጋር ፡ ደርሼ
ድርሻዬን ፡ እወስዳለሁ ፡ ምድሪቷን ፡ ወርሼ

ወደ ፡ ማዶ ፡ እንሂድ ፡ እንሻገር ፡ ሲለኝ (፫x)
ታንኳዬን ፡ ሊገፋት ፡ ንፋስ ፡ ተነሳብኝ (፫x)
ታዲያ ፡ ምን ፡ ጨነቀኝ ፡ ወጀቡ ፡ ቢበዛ (፫x)
ደንግጦ ፡ ይቆማል ፡ ጌታዬ ፡ ሲነሳ (፫x)

ፋንታዬ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማለት ፡ ለኔ
አሃ ፡ ለኔ ፡ አሃሃ ፡ ለኔ (፪x)

ደመናዉ ፡ ከላዬ ፡ ላይ
ገለል ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ፡ ይሄው ፡ ዛሬ
ይሄው ፡ ዛሬ ፡ በድሉ ፡ ጐዳና (፪x)

ምነው ፡ ተከተለኝ ፡ ጠላቴ ፡ ከኋላ (፫x)
ተው ፡ አትከተለው ፡ ሃይ ፡ የሚለው ፡ ጠፋ (፫x)
ቃል ፡ ይዤ ፡ መውጣቴን ፡ ዘንግቶት ፡ ነበረ (፫x)
እኔ ፡ ተሻገርኩኝ ፡ እርሱ ፡ ሰምጦ ፡ ቀረ (፫x)

ፋንታዬ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማለት ፡ ለኔ
አሃ ፡ ለኔ ፡ አሃሃ ፡ ለኔ (፪x)

ደመናዉ ፡ ከላዬ ፡ ላይ
ገለል ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ አረክና (፪x)
አሻገርከኝ ፡ ይሄው ፡ ዛሬ
ይሄው ፡ ዛሬ ፡ በድሉ ፡ ጐዳና (፪x)