መንፈስ ፡ ቅዱስ (Menfes Qedus) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ግራ ፡ አይገባኝም ፡ አንተ ፡ እያለህ ፡ ጐኔ
ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ መድህኔ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)

አልጠፋ ፡ ብሎኝ ፡ ከአእምሮዬ (፪x)
ሁሌ ፡ ያዘምረኛል ፡ ውለታህ ፡ ጌታዬ (፪x)
ቢመዘን ፡ ከእንቁ ፡ ይበልጣል ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው
ዛሬ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኝ ፡ ነው
ምህረት ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው

መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
የእኔ ፡ ነህ ፡ (የእኔ ፡ ነህ) ፡ የእኔ ፡ መሪ ፡ ነህ
የእኔስ ፡ ጌታ ፡ ነህ
(፪x)

የሩቅ ፡ አይደለህም ፡ የቅርቤ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)
የሩቅ ፡ አይደለህም ፡ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)