እዩት ፡ የእኔ ፡ አባት (Eyut Yenie Abat) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አይለወጥም ፡ ፍቅሩ ፡ ትኩስ ፡ ነው ፡ እዩት ፡ የእኔ ፡ አባት
ትከሻው ፡ ሰፊ ፡ እንደሰው ፡ አይደል ፡ ወረት ፡ የለበት
ወረት ፡ የለበት ፡ መሽቶ ፡ ቢነጋ
ደሙ ፡ ገዝቶኛል ፡ እኔ ፡ አለኝ ፡ ዋጋ

አሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኦሆይሆይሆይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ጌታ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ንጉሥ ፡ ነው
አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አምላክ ፡ ነው
አባት ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አባት ፡ ነው

ፍቅሩን ፡ አይቼው ፡ ገረመኝ
ስለኔ ፡ የሰራኀው ፡ ስራ
በመስቀል ፡ ወጥቶ ፡ አዳነኝ
አያልቅም ፡ እኮ ፡ ቢወራ (፪x)

ይሄ ፡ ይሄስ ፡ ፍቅር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ፍቅር
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ፍቅር

አይለወጥም ፡ ፍቅሩ ፡ ትኩስ ፡ ነው ፡ እዩት ፡ የኔ ፡ አባት
ትከሻው ፡ ሰፊ ፡ እንደሰው ፡ አይደል ፡ ወረት ፡ የለበት
ወረት ፡ የለበት ፡ መሽቶ ፡ ቢነጋ
ደሙ ፡ ገዝቶኛል ፡ እኔ ፡ አለኝ ፡ ዋጋ

አሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኦሆይሆይሆይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ጌታ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ንጉሥ ፡ ነው
አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አምላክ ፡ ነው
አባት ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አባት ፡ ነው

ሞገስ ፡ ሆኖኛል ፡ ምህረቱ
ያቆመኝ ፡ ፍቅሩ ፡ ነው ፡ ቤቱ
እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ብዘምር
ይህም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለእግዚአብሄር (፪x)

ይሄ ፡ ይሄስ ፡ ፍቅር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ፍቅር
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ፍቅር

አይለወጥም ፡ ፍቅሩ ፡ ትኩስ ፡ ነው ፡ እዩት ፡ የኔ ፡ አባት
ትከሻው ፡ ሰፊ ፡ እንደሰው ፡ አይደል ፡ ወረት ፡ የለበት
ወረት ፡ የለበት ፡ መሽቶ ፡ ቢነጋ
ደሙ ፡ ገዝቶኛል ፡ እኔ ፡ አለኝ ፡ ዋጋ

አሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኦሆይሆይሆይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ጌታ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ንጉሥ ፡ ነው
አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አምላክ ፡ ነው
አባት ፡ ነው ፡ ለእኔስ ፡ አባት ፡ ነው