በሕይወት ፡ አለሁ (Behiwot Alehu) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ተወራረድኩበት ፡ በዚህ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ
አይጥለኝም ፡ አልኩኝ ፡ እኔንም ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ፡ (ኦሆ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ)
የድሮ ፡ ቃልኪዳን ፡ በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
ፎከርኩኝ ፡ በአምላኬ ፡ አይተወኝም ፡ ከቶ ፡ (ኦሆ ፡ እኔን ፡ ከቶ)

እንደ ፡ ዓይኑ ፡ እኔን ፡ ሲያይ
ገረመኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ
ምህረቱ ፡ ገንኖ ፡ ነው ፡ ለካ
ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ጨለማ (፪x)

ዞር ፡ ዞር ፡ አልኩና ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ (ወደ ፡ ግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ)
ከፊትም ፡ ከኋላም ፡ ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ ፡ (ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ)
ዓይኖቼን ፡ ሳነሳ ፡ ወደ ፡ የዋሁ ፡ ጌታ ፡ (ወደ ፡ ጀግናው ፡ ጌታ)
ችግሬን ፡ አጣሁት ፡ እሱን ፡ ባየሁ ፡ ለታ ፡ (እሱን ፡ ባየሁ ፡ ለታ)

ጌታ ፡ እንደሌለው ፡ እንደሌለው
እንደማንም ፡ እኔስ ፡ አይደለሁም
ቀና ፡ ስል ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ወደ ፡ አምላኬ
ልመናዬን ፡ ሰማኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)

በቅጡ ፡ አውቀዋለሁ ፡ የኔን ፡ ጌታ
ያሻግራል ፡ ቃሉማ ፡ መልካም ፡ ቦታ
ሰንቆም ፡ ላከልኝ ፡ መልሴን ፡ ፈጥኖ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በቃ ፡ ብሎ (፪x)

ምንድነው ፡ ሚሰማው ፡ በከተማው ፡ ወሬ
ሞቷል ፡ አትበሉ ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ ዛሬ (ኦሆ ፡ አለሁ ፡ ዛሬ)
እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ሃሳብ ፡ ወደ ፡ ግብጽ ፡ ቢወርድም
ህልሙ ፡ ሳይፈጸም ፡ ባለራዕይ ፡ አይሞትም (በፍጹም ፡ አይሞትም)

እንደ ፡ ዓይኑ ፡ እኔን ፡ ሲያይ
ገረመኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ
ምህረቱ ፡ ገንኖ ፡ ነው ፡ ለካ
ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ጨለማ (፪x)