በአንተ ፡ ነው (Bante New) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ማልጄ ፡ ደግሞ ፡ ስነሳ ፡ ስለውለታህ ፡ ላነሳሳ
ሌቱም ፡ አልበቃ ፡ አልበቃ ፡ አለኝ
ቀኑም ፡ እጥር ፡ እጥር ፡ አለብኝ
የተደረገልኝ ፡ ራሴው ፡ ነው ፡ የማውቀው
ዛሬ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ነው

ሳስበው ፡ የትላንቱን ፡ (አሃሃ)
አሰቃቂ ፡ መንገዱን ፡ (ኦሆሆ)
በፀጋህ ፡ ደገፍከኝና ፡ (አሃሃ)
ገረመኝ ፡ አለፍኩትና (፪x)

በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

እረካሁ ፡ ከእጅህ ፡ ጠጥቼ ፡ (አሃሃ)
ወጣሁት ፡ ጉልበት ፡ አግኝቼ ፡ (አሃሃ)
አልቀረሁ ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ (አሃሃ)
አትወድም ፡ ሰው ፡ እንዲጐዳ ፡ (አሃሃ) (፪x)

በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

አንተ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ነዉ
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ነዉ

ቆጥሬው ፡ ተናግሬው ፡ (አሃሃ)
ከውስጤ ፡ የማይወጣው ፡ (አሃሃ)
ጌትዬ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ (አሃሃ)
ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ነው ፡ (አሃሃ) (፪x)

በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)