አለኝ ፡ የምለው (Alegn Yemelew) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 4.jpg


(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

የልብ ፡ ልቤን ፡ ላውጣው ፡ እስቲ ፡ ልናገር
ጌታ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ የሚነገር
እርሱ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ስሙኝ ፡ የሚነገር (፪x)

የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ የራሴ
መተኪያ ፡ የሌለህ ፡ ኢየሱሴ
ከስንቱ ፡ ቦታ ፡ ስንቱን ፡ አሻግረህ
ሊዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x)

ፀሐዩ ፡ ሲጠልቅ ፡ ጨለማው ፡ ሲመጣ
ንጉሥ ፡ ንጉሥን ፡ ሽሮ ፡ አንዱ ፡ በአንዱ ፡ ፈንታ
ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ጉልበቱ ፡ ሊፈታ
የማትለዋወጥ ፡ የማትቀያየር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ(፪x)

አለኸኝ ፡ የምለው
የእኔው ፡ ነህ ፡ የምለዉ
አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ
አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፪x)

የልብ ፡ ልቤን ፡ ላውጣው ፡ እስቲ ፡ ልናገር
ጌታ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ የሚነገር
እርሱ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ስሙኝ ፡ የሚነገር (፪x)

የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ የራሴ
መተኪያ ፡ የሌለህ ፡ ኢየሱሴ
ከስንቱ ፡ ቦታ ፡ ስንቱን ፡ አሻግረህ
ሊዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x)

ወንዝ ፡ አያሻግርም ፡ የቅርብ ፡ ወዳጅ ፡ ሆኖ
ፍቅር ፡ ዛሬ ፡ የለም ፡ ይላል ፡ ቀረ ፡ ድሮ
ሁኔታ ፡ ሲለወጥ ፡ ከአለበት ፡ ቦታ
የማትለዋወጥ ፡ የማትቀያየር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ(፪)

አለኸኝ ፡ የምለው
የእኔው ፡ ነህ ፡ የምለዉ
አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ
አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፪x)

አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፫x)