አላየሁህም (Alayehuhem) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Lyrics.jpg


(2)

በአምባው ላይ ተቀምጠህ
(Beambaw Lay Tekemteh)

ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አላየሁህም አንድ ቀን ስትከዳኝ
አላየሁህም ከፊቴ ስትርቀኝ
እግዚአብሄር እንዳንተ ማንም የለም እኮ (2x)

አይኖቼ ማዳንህን አዩ ያ መከራዬ ተረሳ
እግዚአብሄር ሲደርስልኝ ለሊቱ ባንዳፍታ ነጋ
በፊቱ ሞገስን አገኘሁ ልመናዬ ተሰማልኝ
የረሀቡ ዘመን አበቃ ገበታን አዘጋጀልኝ

ከልቤ ላመስግንህ ከልቤ (4)
አላየሁህም አንድ ቀን ስትከዳኝ
አላየሁህም ከፊቴ ስትርቀኝ
እግዚአብሄር እንዳንተ ማንም የለም እኮ (2x)

ታማኝነትህ በዝቶልኝ ሳትቆጥብ ከፍ አደረከኝ
አስኬድከኝ በከፍታው ላይ ጠላቴ በአይኑ እንዲያይ
ለኔ እንዳንተ ማንም የለም ጉልበቴ ነህ የኔ ጌታ
በሰጠኸኝ እድሜ ዘመን ላክብርህ ሁሌ ጠዋት ማታ

ከልቤ ላመስግንህ ከልቤ (4)
አላየሁህም አንድ ቀን ስትከዳኝ
አላየሁህም ከፊቴ ስትርቀኝ
እግዚአብሄር እንዳንተ ማንም የለም እኮ (2x)

እግዚአብሔር እረኛዬ ነህ በለምለም መስክ እሄዳለሁ
ውሃ ባለበት መንደር ውስጥ መኖሪያዬ አድርጌአለው
ንጉሴ የሆከውን አንተን በልቤ ላይ ሾሜሃለሁ
ለዘላለም በቤትህ ውስጥ ተደላድዬ ኖራለሁ

ከልቤ ላመስግንህ ከልቤ (4)
አላየሁህም አንድ ቀን ስትከዳኝ
አላየሁህም ከፊቴ ስትርቀኝ
እግዚአብሄር እንዳንተ ማንም የለም እኮ (2x)