የራራልኝ (Yeraralegn) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ እጄን ፡ አጥብቆ ፡ የያዘኝ
ዘር ፡ ባልተዘራበት ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በፍቅሩ ፡ ያባበለኝ
ጊንጡን ፡ ረጋግጦልኝ ፡ እባቡም ፡ እንዳይነድፈኝ
እንባዬን ፡ በእጁ ፡ ጠራርጐ ፡ አባት ፡ ልሁንሽ ፡ ያለኝ

አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ
ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል
በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x)
ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ
ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ
የሞተው ፡ ይነሳ ፡ የለም ፡ ወይ
ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ
ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ
አልአዛርስ ፡ ቆሞ ፡ የለም ፡ ወይ

በአመት ፡ መሃል ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማይለወጥ ፡ ደግ ፡ ጌታ
ተስፋ ፡ ሲጨልም ፡ ቀን ፡ ሲመሽ ፡ የሚደርስ የማታ ፡ ማታ
ስሙን ፡ ጠርቼ ፡ አላፈርኩ ፡ አንገት ፡ አልደፋሁ ፡ በዘመኔ
ህያው ፡ ምስክር ፡ ያረገኝ ፡ ሳይርቀኝ ፡ ቆሞ ፡ ከጐኔ

አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ
ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል
በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x)
ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ
ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ
የሞተው ፡ ይነሳል ፡ የለም ፡ ወይ
ይችላል ፡ ይችላል ፡ ብያለሁ ፡ በነገሬ ፡ ላይ
ቃል ፡ ከአፉ ፡ ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ከሠማይ
አልአዛርስ ፡ ቆሞ ፡ የለም ፡ ወይ

የደረቀ ፡ አጥንት ፡ ነው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው
የሸተተ ፡ ሬሳ ፡ ነው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው
ትቼዋለሁ ፡ ቀብሬው ፡ ግን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው
ያወጣዋል ፡ በጊዜው ፡ አዎ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው

መርከብ ፡ ተሰብሮ ፡ በተሰበረው
መድረስ ፡ ከቻለ ፡ ያ ፡ የእምነት ፡ ሰው
ዛሬም ፡ በቤቴ ፡ ይሄ ፡ ይሆናል
አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል
አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል
አልጠረጥርም ፡ ጌታ ፡ ይችላል
አልጠረጥርም ፡ ጌታ ፡ ይችላል
አልጠረጥርም ፡ እርሱ ፡ ይችላል

አዝ፦ የራራልኝ ፡ የደገፈኝ ፡ ሰዎች ፡ ሲረሱኝ ፡ ያስታወሰኝ
ዛሬም ፡ ሊረዳኝ ፡ መች ፡ ይሰለቻል
በእርሱ ፡ ተረድቶ ፡ ማን ፡ ወድቆ ፡ ያውቃል (፪x)