Addisalem Assefa/medanie benetsa

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

{{AlbumPage |ዘማሪ=addisalem assefa |Artist=addisalem assefa |አልበም=medanie benetsa |Album=medanie benetsa

መዳኔ በነፃ ኣደረገው መትረፌ በነፃ ኣደረገው ምንም ክፍያ ስለማይመጥነው ምንም ስጦታ ስለማይመጥነው

የምስራች ኣሃሃ ሰፈሬ ድረሰ ኢየሱስ መጣ ከቤቴ ሂወቴ ታደሰ

ያለምንም ውጣ ውረድ ነው ኦሆሆ ኢየሱስ ኣምላኬ የሆነው ያለምንም ድካም ጥረት ነው ኦሆሆ ኢየሱስ ኣባቴ የሆነው

ዘሬና ጎሳየን አለየ መጥቶ ሲያድነኝ የጠፋ በሚፈልግ መንፈስ እንዲያው ወደደኝ አባብሎ ልቤን አሸፍቶ መረብ አስጥሎኝ እስከሞት የታዘዘበትን መንገድ አሳየኝ

እሱ ነው የፍቅር ፊደል ሀሁ ያስተማረኝ እሱ ነው ሰው ሳይቀበለኝ የተቀበለኝ እሱ ነው ከነማንነቴ እቅፍ ያረገኝ ኢየሱስ የምተርክበት ምን ቃላት ላገኝ

ለከዳው ለሓጢአተኛው ወዳጅ ለምስኪኑ ዳኛ እንድያው አዋዋሉ ሳይቀር ሆኖ ዝቅተኛ ተዋርዶ ራሱን ባዶ አድርጎ ሆኖ ትሁተኛ ለሂወቴ ምሳሌ የሆነኝ ኢየሱስ ነው ብቸኛ

እሱ ነው ለሰዎች ባሳይ የማላፍርበት እሱ ነው የማወራው ወጌ ከሰው ስጫወት እሱ ነው የምወተውተው የነፍሴ ጭሆት እሱ ነው ዘላለም ስባርከው ልኑር ዘሬ ይገዛለት