ተሸክመህ (Teshekemeh) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ተሸክመህ ደከመኝ የማትለኝ
ከማንም ይልቅ አብልጠህ ምትጠጋኝ
የማትከዳ የክፉ ቀን ወዳጄ
ወደድከኝ ምንም ሳይኖር ከእጄ
     አንተ አንተ ግን ያው አንተ ነህ /4
     በከፍታ ያው አንተ ነህ
     በዝቅታም ያው አንተ ነህ
     ከእጄ ሳጣ ያው አንተ ነህ
    ለዘለዓለም ወዳጄ ነህ

ብዙዎች ነበሩ መመረጥ የተገባቸው
አንተ ግን ምህረትህ እይታህ መች እንደ ሰው
በጣም ደካማን ሰው ስትፈልግ አገኘኸኝና
መንፈስህ ሸላልሞ አቆመኝ አበረታኝና
        የማውቀው መወደዴን ነው /2
        ካንተ ውጭ ትምክህት የለኝም ከእኔ የምለው

ነፋስ በሞላበት ውድማ ወድቄ አይተኸኝ
ከበህ ተጠንቅቀህ አሙቀህ ብርድ እንዳያገኘኝ
ንስር ጫጩቶቿን በክንፏ እንደምትደብቅ
በጉያህ ሸሽገህ አኖርከኝ እንዳልሳቀቅ
        የማውቀው መወደዴን ነው /2
        ካንተ ውጭ ትምክህት የለኝም ከእኔ የምለው
 አመሰግንሃለሁ /3
 ክብርን በአንተ አይቻለሁ