ስንት ፡ ጊዜ (Sent Gizie) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አንድ ፡ ነገር ፡ በጣም ፡ ገብቶኛል ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
የዛለው ፡ በአንተ ፡ ሲበረታ ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ
ተቆትተህ ፡ በዛው ፡ አትቀርም ፡ እስከ ፡ መጨረሻው
ቢወድቅም ፡ ይነሳል ፡ ፃዲቁ ፡ ስላለው ፡ መድረሻ

አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን
ከደንከው ፡ በብርሃን
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ
ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x)

ያንን ፡ ጭጋግ ፡ ደመናውን
ያን ፡ በረሃ ፡ ሃሩሩን
በአንተ ፡ ጉልበት ፡ አልፌዋለሁ
በማሳለፍ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማነው
ያን ፡ ኃጢያቴን ፡ ቁሻሻውን
ያንን ፡ ልብሴን ፡ እድፋሙን
ቀይረህ ፡ ከሞት ፡ ወጥቻለሁ
በማስወጣት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማነው

አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን
ከደንከው ፡ በብርሃን
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ
ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x)

ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ማነሳሳህ ፡ ደጋግሜ
በተከበበው ፡ ከተማማ ፡ ለእኔ ፡ ይገርመኛል ፡ መቆሜ
ስለዚህ ፡ በምሥጋና ፡ ልውጣ ፡ ያረክልኝን ፡ ቆጥሬ
ሳላስበው ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አይቻለሁና ፡ ከብሬ

አዝ፦ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አነሳኸኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቅም ፡ ሆንከኝ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ጨለማዬን
ከደንከው ፡ በብርሃን
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ስደክምብህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ያዘኝ ፡ ፀጋህ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ ከጠላት ፡ ዛቻ
ከለለኝ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ (፭x)

አባትዬ ፡ ኢየሱስዬ
አልከሰርኩም ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)

እኔ ፡ አንተን ፡ ብዬ (፬x)