From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይተወኝ (፪x)
ሸምበቆ ፡ አይደል ፡ ስደገፈው ፡ ሚያንሸራትተኝ
መቼም ፡ አይተወኝ
መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ (፪x)
ሰው ፡ አይደል ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥሎ ፡ ግራ ፡ የሚያጋባኝ
መቼም ፡ አይረሳኝ
መቼም ፡ አይተወኝ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ
መቼም ፡ አይተወኝ ፡ ገንዘብ ፡ እኮ ፡ ነኝ (፪x)
ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ገና ፡ ገና ፡ ሳለሁኝ
እዛው ፡ ውስጥ ፡ እያለሁኝ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ በስም ፡ ያወቀኝ
የጸጉሬ ፡ ልክ ፡ እንኳን ፡ በእርሱ ፡ የተቆጠረ ፡ ነው
ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይተወኝም ፡ ኪዳኑ ፡ ጽኑ ፡ ነው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ጐልያድን ፡ ሳልፈራው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ዮርዳኖስን ፡ ሳልሰማው
ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ
ሸለቆዬን ፡ ይሞላዋል ፡ ደመናም ፡ ሳላይ
በእኔ ፡ ሳይሆን ፡ በእርሱ ፡ ሰዓት ፡ ተራምዶ ፡ ይደርሳል
ነገሬን ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ ሰርቶ ፡ ይጨርሳል
አዝ፦ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይተወኝ (፪x)
ሸምበቆ ፡ አይደል ፡ ስደገፈው ፡ ሚያንሸራትተኝ
መቼም ፡ አይተወኝ
መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ (፪x)
ሰው ፡ አይደል ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥሎ ፡ ግራ ፡ የሚያጋባኝ
መቼም ፡ አይረሳኝ
መቼም ፡ አይተወኝ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ
መቼም ፡ አይተወኝ ፡ ገንዘብ ፡ እኮ ፡ ነኝ (፪x)
የሠማያት ፡ ወፎች ፡ እንኳን ፡ ሳይዘሩ ፡ ሳያጭዱ
ይኸው ፡ ይኖሩ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ በእርሱ ፡ እየተረዱ
ይልቁንስ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ በደም ፡ ተገዝቼ
እንዴት ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር ፡ ከክፉ ፡ ገብቼ
ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ጐልያድን ፡ ሳልፈራው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልከው ፡ ዮርዳኖስን ፡ ሳልሰማው
ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ በስራ ፡ ላይ
ሸለቆዬን ፡ ይሞላዋል ፡ ደመናንም ፡ ሳላይ
በእኔ ፡ ሳይሆን ፡ በእርሱ ፡ ሰዓት ፡ ተራምዶ ፡ ይደርሳል
ነገሬን ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ ሰርቶ ፡ ይጨርሳል
ጨለማው ፡ ሲመስል ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ አይጨልምበትም
አሃሃሃሃ ፡ አይጨልምበትም
ነገሬን ፡ ሊሰራ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ በውበት
አሃሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ በውበት
የሰዎችን ፡ ልጆች ፡ ከልቡ ፡ መቼ ፡ ያስጨንቅና
አሃሃሃሃ ፡ መቼ ፡ ያስጨንቅና
ዘመናት ፡ ያመጣል ፡ ሊምላ ፡ አፉን ፡ በምሥጋና
አሃሃሃ ፡ አፉን ፡ በምሥጋና
ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ
የርስቴ ፡ ጌታ ፡ ደራሼ ፡ እርሱ ፡ ነው (፬x)
ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ
የርስቴ ፡ ጌታ ፡ ደራሼ ፡ እርሱ ፡ ነው (፬x)
|