From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከአፌ ፡ የማይጠፋ ፡ የማልረሳው ፡ የማልረሳው
ከአፌ ፡ የማይጠፋው ፡ የማልተወው ፡ የማልተወው
ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ነው (፬x)
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x)
በሕይወት ፡ ለመኖር ፡ የሚያስችለኝ
ከሠማይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶልኝ
ነው ፡ እንጂ ፡ በቤቱ ፡ መሠንበቴ
መቼ ፡ በኃይልና ፡ በብርታቴ ፡ አሃ ፡ በብርታቴ
እርሱ ፡ ነው ፡ ከደሜ ፡ ያጠራኝ
አፍረቴን ፡ ሸፍኖ ፡ ያነሳኝ
እርቃኔን ፡ በመጎናጸፍያው ፡
ደብቆ ፡ ያከበረኝ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ አሃ ፡ እርሱ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ጎትጓች ፡ አልፈልግም ፡ አምላኬን ፡ ለማመስገን ፡ ጌታዬን ፡ ለማመስገን
በእርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሻገርኩት ፡ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ክፉ ፡ ቀን (፪x)
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x)
በንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ተቀምጬ ፡ ከሕይወት ፡ እንጀራው ፡ እንድበላ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ይሁን ፡ ተብሎ ፡ ሲነገር ፡ ሲወራ (፪x)
በትልቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተወድጄ ፡ ከውዳቂ ፡ ስፍራ ፡ ተነስቼ
በፊቱ ፡ ልቆም ፡ ዘንድ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
እስከዚህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ የወደደኝ ፡ አሃሃ ፡ የወደደኝ
ስለዚህ ፡ ጎትጓች ፡ አልፈልግም ፡ አምላኬን ፡ ለማመስገን ፡ ጌታዬን ፡ ለማመስገን
በእርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሻገርኩት ፡ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ክፉ ፡ ቀን (፪x)
ከአፌ ፡ የማይጠፋ ፡ የማልረሳው ፡ የማልረሳው
ከአፌ ፡ የማይጠፋው ፡ የማልተወው ፡ የማልተወው
ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ነው (፬x)
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x)
|