ህዝቤን ፡ ስጠኝ (Hezbien Setegn) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ አንተ ፡ የልቤ ፡ ሆይ (፪x)
አንዴ ፡ አስበኝና ፡ ማዳንህን ፡ ልይ (፪x)
ክንዱ ፡ ወዴት ፡ አለ ፡ ብሎ ፡ ለሚለኝ (፪x)
ለህዝብህ ፡ ጥያቄ ፡ ባክህ ፡ መልስ ፡ አርገኝ (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ
እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ
የምድርን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x)
ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ
የፈሰሰው ፡ እንባ ፡ ቢታበስ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ቢታደስ
ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ
ተራራው ፡ በፊትህ ፡ ቢናወጥ ፡ ስምህ ፡ ለጠላቶች ፡ ቢገለጥ

መልሰኛ ፡ ፈውስ ፡ አድርገህ ፡ ለሃገሬ ፡ ህመምተኛ
ቀድሰኛ ፡ እንድሆን ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ተቆጥተህ ፡ ፊትህን ፡ አትደብቅብኝ
ደክሞኝ ፡ ሳለ ፡ ጠላቴ ፡ እንዳይወድቅብኝ

በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ የቆመ ፡ ለእንጀራ ፡ ያልኖረ (፪x)
የቤትህ ፡ ቅናት ፡ የሚበላው ፡ ስሙን ፡ የቀበረ (፪x)
የልብህን ፡ ቁጣ ፡ ትኩሳት ፡ የሚያበርድልህ (፪x)
እንዲህ ፡ ዐይነት ፡ ጨካኝ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ኃይልህን ፡ ሞልተህ (፪x)
ከዚያ ፡ በኋላማ ፡ ስምህን ፡ አክብረህ ፡ ትመላለሳለህ ፡ መስርአት ፡ ሳይከብድህ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ
እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ
የህዝቤን/የምድሬን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x)
ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ
የፈሰሰው ፡ እንባ ፡ ቢታበስ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ቢታደስ
ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ
ተራራው ፡ በፊትህ ፡ ቢናወጥ ፡ ስምህ ፡ ለጠላቶች ፡ ቢገለጥ

መልሰኛ ፡ ፈውስ ፡ አድርገህ ፡ ለሃገሬ ፡ ህመምተኛ
ቀድሰኛ ፡ እንድሆን ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ተቆጥተህ ፡ ፊትህን ፡ አትደብቅብኝ
ደክሞኝ ፡ ሳለ ፡ ጠላቴ ፡ እንዳይወድቅብኝ

በምድሬ ፡ እንዳትሰራ ፡ እንዳትከብር ፡ የከለከልኩኝ (፪x)
አንካሳ ፡ የሕይወት ፡ ማንነት ፡ ያለኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ (፪x)
አሁን ፡ ግን ፡ በምህረት ፡ ዐይንህ ፡ አይተኸኝ (፪x)
የተጨነቀውን ፡ ህዝብህን ፡ ስጠኝ (፪x)
ኢየሱስ ፡ እባክህ ፡ ነክቼህ ፡ ንካኝ
ኃይልህ ፡ እስኪወጣ ፡ ልበልህ ፡ ሙጥኝ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x)
አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ
እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ
የህዝቤን/የምድሬን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x)

ህዝቤን ፡ ስጠኝ ፡ እንደፈቃድህ ፡ አውለኸኝ ፡ ህዝቤን ፡ ስጠኝ
ህዝቤን ፡ ስጠኝ ፡ በቅድስናህ ፡ አውለከኝ ፡ ህዝቤን ፡ ስጠኝ
ህዝቤን ፡ ስጠኝ (፬x)