ገናና ፡ ነህ (Genana Neh) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አዝገናና ፡ ገናና ፡ ነው (፬x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው

ኧረ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ላምልከው
እንዴት ፡ እንዴት ፡ ላምልከው (፫x)
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባዋል ፡ ክብሬን ፡ ብጥል ፡ ያንስበታል
ሞቴን ፡ ለወሰደ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ አለኝ ፡ በዕልልታ (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ በዕልልታ (፬x)

እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ባሕሩን ፡ ከፈለ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ፈረሰኛ ፡ ጣለ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ ግብጽን ፡ ተበቀለ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ያለ

ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና
ዙፋኑ ፡ የጸና (፬x)

አዝገናና ፡ ገናና ፡ ነው (፬x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው

እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሞትን ፡ አሸነፈ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ጨለማ ፡ ገፈፈ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና
ዙፋኑ ፡ የጸና (፬x)

አዝገናና ፡ ገናና ፡ ነው (፬x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ልቤ ፡ የሾመው
በአማልክቶች ፡ ሁሉ ፡ መሃል ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው

ከሁሉ ፡ በላይ (፫x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የበላይ (፪x)
ከሁሉ ፡ በላይ (፫x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኤልሻዳይ (፬x)

ኧረ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ላምልከው
እንዴት ፡ እንዴት ፡ ላምልከው (፫x)
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባዋል ፡ ክብሬን ፡ ብጥል ፡ ያንስበታል
ሞቴን ፡ ለወሰደ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ አለኝ ፡ በዕልልታ (፪x)
አምልኮ ፡ አለኝ ፡ በዕልልታ (፬x)