ፍጻሜ ፡ የሌለህ (Fetsamie Yelieleh) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አዝ፦ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ዘለዓለም ፡ ነው ፡ ብዛትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የጸና ፡ ነው ፡ መንግሥትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ትገዛለህ ፡ በህይልህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የማይፈራህ ፡ ማነው ፡ የማያከብርህ
ሁሉም ፡ ተንበርክኮ ፡ ይሰግዳል ፡ ፊትህ (፪x)

ስምህ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ አሜን ፡ የሆንከው
በምድር ፡ ክበባት ፡ ላይ ፡ የምትረግጠው
እንዲህን ፡ እንደዚያ ፡ የማትባለው
ታላቅነትህን ፡ እንዴት ፡ ልግለጸው (፪x)

ድንቅ ፡ ተዐምራትን ፡ በቃልህ ፡ የምትሰራ
የሌለውን ፡ ነገር ፡ በስም ፡ የምትጠራ
እስትንፋስን ፡ ሰጥተህ ፡ የምታኖረው
ያለና ፡ የሚኖር ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህና (፫x)
ለስምህ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና (፬x)
የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)
የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ ፡ የሆነ (መሥጋና)
የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)
ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ፡ ያለው (ምሥጋና)

አዝ፦ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ዘለዓለም ፡ ነው ፡ ብዛትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የጸና ፡ ነው ፡ መንግሥትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ትገዛለህ ፡ በህይልህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የማይፈራህ ፡ ማነው ፡ የማያከብርህ
ሁሉም ፡ ተንበርክኮ ፡ ይሰግዳል ፡ ፊትህ (፪x)

የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አየመረመር
የለህም ፡ ጓደኛ ፡ የሚፎካከር
በአመታት ፡ መሃል ፡ የማታረጅ ፡ ጌታ
ፍጥረት ፡ ይስገድልህ ፡ በጠዋት ፡ በማታ (፪x)

በገናው ፡ ይደርደር ፡ ከበሮው ፡ ይመታ
ምድር ፡ እልል ፡ ትበል ፡ ይነፋ ፡ እምቢልታ
በዜማ ፡ እቃ ፡ ሁሉ ፡ ስምህ ፡ ከፍ ፡ ይበል
ድንቅ ፡ መካር ፡ ጌታ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ኃያል (፪x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህና (፫x)
ለስምህ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና (፬x)
የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)
የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ ፡ የሆነ (መሥጋና)
የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)
ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ፡ ያለው (ምሥጋና)

አዝ፦ ፍጻሜ ፡ የሌለህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ዘለዓለም ፡ ነው ፡ ብዛትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የጸና ፡ ነው ፡ መንግሥትህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
ትገዛለህ ፡ በህይልህ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ነህ (፪x)
የማይፈራህ ፡ ማነው ፡ የማያከብርህ
ሁሉም ፡ ተንበርክኮ ፡ ይሰግዳል ፡ ፊትህ (፪x)

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህና (፫x)
ለስምህ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና (፬x)
የከበረ (ምሥጋና) ፣ የገነነ (ምሥጋና)
የገዘፈ (ምሥጋና) ፣ ብዙ ፡ የሆነ (መሥጋና)
የምትወደው (ምሥጋና) ፣ ምታሸተው (ምሥጋና)
ይሁንልህ (ምሥጋና) ፣ ሞገስ ፡ ያለው (ምሥጋና)

ምሥጋና (፱x)