እስኪ ፡ አንድ ፡ ሰው (Eski And Sew) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ
ይገባዋልና (፫x)
አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ
ይገባዋልና (፫x)

እስቲ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ያለው (፬x)

ኢየሱስ ፡ በሕይወቱ ፡ የሆነው ፡ ብቸኛ
አመልካለሁ ፡ የሚል ፡ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ
ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ
ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ
ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ
ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ

አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ
ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ
ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ
ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስርአት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ

የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ (፪x)

አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ የተደረገለት
አሃሃሃ ፡ ድቅድቅ ፡ ጨለማው ፡ የተገፈፈለት
አሃሃሃ ፡ እድፋሙ ፡ ልብሱ ፡ የተቀየረለት
አሃሃሃ ፡ ሃማ ፡ እያየ ፡ የተፈረደለት

አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ
ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ
ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ
ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ

እኔ ፡ አለበኝ ፡ ውለታው ፡ እኔ ፡ አለብኝ
እኔ ፡ አለብኝ ፡ ውለታው ፡ ዝምበል ፡ አትበሉኝ (፪x)

አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ፀሐይ ፡ የወጣለት
አሃሃሃ ፡ የተማሰ ፡ ጉድጓድ ፡ የተደፈነለት
አሃሃሃ ፡ ሟርቱ ፡ ድግምቱ ፡ የተረገጠለት
አሃሃሃ ፡ ብርቱ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተሟገተለት

አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ
ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ
ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ
ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ

አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ውለታ ፡ ያለበት
አሃሃሃ ፡ ሰባራ ፡ ልቡ ፡ የተጠገነለት
አሃሃሃ ፡ ሞቱ ፡ ሲታወጅ ፡ ትንሳኤ ፡ የሆነለት
አሃሃሃ ፡ ጌታ ፡ ነገሩን ፡ የገለበጠለት

አዝ፦ ከአመድ ፡ ላይ ፡ የተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ያለው ፡ እንደኔ
ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ የሚል ፡ ካለ ፡ ይቁምልኝ ፡ ከጐኔ
ክብሬን ፡ ስሜን ፡ ብጥልልህ ፡ እብድ ፡ አትበሉኝ
ከጠላቴ ፡ ጽኑ ፡ እስራት ፡ የተፈታሁ ፡ ነኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ አትታዘቡኝ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ዝም ፡ በይ ፡ አትበሉኝ

አይቋረጥም ፡ ከጀመርኩት ፡ ምሥጋናዬ
እጨምራለሁ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታዬ
ይገባዋልና ፡ ይገባዋልና
እስቲ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ያለው (፬x)

ኢየሱስ ፡ በሕይወቱ ፡ የሆነው ፡ ብቸኛ
አመልካለሁ ፡ የሚል ፡ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ
ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ
ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ
ይተባበረኛ ፡ ይተባበረኛ
ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ ፤ ቀኝ ፡ እጁን ፡ ይስጠኛ