እኔስ ፡ ኢየሱስ (Enies Eyesus) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 7:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ህጉን ፡ ልተግብረው ፡ እንጂ ፡ በሕይወቴ ፡ ቃሉን ፡ ልኑረው
ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ ይፈጸማል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለው
እራስ ፡ እንጂ ፡ ጅራት ፡ ላልሆን ፡ ቃሉ ፡ እንደሚለው
በስሙ ፡ የተጠራሁ ፡ ሰው ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ የኪዳኑ ፡ ሰው (፪x)

አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም (፪x)
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም (፪x)

እቸኩላለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
ወደ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ገና
በዐይኔ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
የጌታን ፡ ተአምር ፡ ገናና (፪x)

እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ ፈጥኖ ፡ አንስቶኛል ፡ ከውድቀት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ (፬x)

ክንዱን ፡ ተማምኖ ፡ እኔን ፡ ሲጠራ ፡ አሃሃ ፡ እኔን ፡ ሲጠራ (፪x)
ያልተጸጸተ ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ ፡ አሃሃ ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ (፪x)
መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ አቅንቶልኛል ፡ አሃሃ ፡ አቅንቶልኛል (፪x)
ለብዙ ፡ ክብር ፡ ይፈልገኛል ፡ አሃሃ ፡ ይፈልገኛል (፪x)
ቃሉን ፡ ሊያጸና ፡ ሊደግፈኝ ፡ አሃሃ ፡ ሊደግፈኝ (፪x)
ከፊቴ ፡ ወጥቶ ፡ አይዞሽ ፡ ካለኝ ፡ አሃሃ ፡ አይዞሽ ፡ ካለኝ (፪x)
ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ልፍራ ፡ ልኡሉን ፡ ይዤ ፡ አሃሃ ፡ ልኡሉን ፡ ይዤ (፪x)
ልጓደድ ፡ እንጂ ፡ ስሙን ፡ መዝዤ ፡ አሃሃ ፡ ስሙን ፡ መዝዤ (፪x)

እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ መቆም ፡ አልሻም ፡ መዘግየት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ (፬x)

አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም (፪x)
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም (፪x)

እቸኩላለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
ወደ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ገና
በዐይኔ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
የጌታን ፡ ተአምር ፡ ገናና (፪x)

የሚዘጋና ፡ የሚከፍተው ፡ አሃሃ ፡ የሚከፍተው (፪x)
መወርወሪያውን ፡ የሰበረው ፡ አሃሃ ፡ የሰበረው (፪x)
ጠላቴን ፡ ሁሉ ፡ ተጣልቶልኛል ፡ አሃሃ ፡ ተጣልቶልኛል (፪x)
ተከናወኚ ፡ ሂጂ ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ ፡ ሂጂ ፡ ብሎኛል (፪x)
እንደመጣው ፡ ቃል ፡ አሜን ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ አሜን ፡ ብያለሁ (፪x)
ባሕር ፡ ተከፍሎ ፡ እሻገራለሁ ፡ አሃሃ ፡ እሻገራለሁ (፪x)
ሁሉን ፡ በሚያስችል ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ ፡ አሃሃ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ (፪x)
እንዴት ፡ ብትሉ ፡ ኃይሌ ፡ የጌታ ፡ ነው ፡ አሃሃ ፡ ኃይሌ ፡ የጌታ ፡ ነው (፪x)

እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ መቆም ፡ አልሻም ፡ መዘግየት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ (፬x)

አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም (፪x)
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም (፪x)