እሄዳለሁ (Ehiedalehu) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ
(Yamelete Enie Negn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ማዕበሉ ፡ ለምን ፡ ገፋኝ ፡ አልልም ፡ ይግፋኝ
ወጀቡ ፡ ለምን ፡ ነካኝ ፡ አልልም ፡ ይንካኝ (፪x)

አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x)

ሁሉን ፡ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ (፫x)
የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ
ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)

ድንጋዩን ፡ ሁሉ ፡ እንቅፋቱን
ከፊቴ ፡ ጠርጐ ፡ ተራራውን
በእኔ ፡ ችሎ ፡ የማልችለውን
አለማምዶኛል ፡ ተዐምራቱን (፪x)

ማቆም ፡ ይችላል ፡ ማዕበሉን
ማዘዝ ፡ ይችላል ፡ ንፋሳቱን
ባያቆመውም ፡ አውራቂሱን
እሻገራለሁ ፡ ይዤ ፡ ቃሉን (፪x)

ቁዘማውን ፡ ይውሰደው
እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው
ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ (፪x)

አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x)

የሚሆንለት ፡ እርሱ ፡ እንዳለው
የሚቆምለት ፡ እንዳሰበው
የዕድሜህን ፡ ቁጥር ፡ የሚያሰላው
የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ነው (፪x)

ስለዚህ ፡ ለምን ፡ ሽንፈትን ፡ ላውራ
ለትንሽ ፡ ነገር ፡ እንደተጠራ
ልታመን ፡ እንጂ ፡ ኃይል ፡ ባለው
ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ በተባለው (፪x)

ቁዘማውን ፡ ይውሰደው
እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው
ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ (፪x)

አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x)

ኦሮምኛ . (3) .

አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x)