ዘመን ፡ መጣ (Zemen Meta) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 2.jpg


(2)

ሰባሪው ፡ ጌታ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቷል
(Sebariw Gieta Kefitie Wettual)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ሞቴን ፡ በሕይወት ፡ ቀይሮ ፡ ነገሬን ፡ ሊገለብጥ
በጭንቀቴ ፡ ሊያሰፋ ፡ ከፍታን ፡ ለእኔ ፡ ሊሰጥ
አዎ ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ ከፊቴ ፡ ፋሬስ ፡ ብዬ ፡ የምጥስበት
የያዘኝ ፡ ዳግም ፡ ላይዘኝ ፡ ሰብሬ ፡ የምወጣበት (፪x)

ሰባሪው ፡ ጌታ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቷል
አማሌቅ ፡ ፈርቶ ፡ መንገዴን ፡ ለቋል
ክረምቱ ፡ አልፎ ፡ ጭጋጉ ፡ በኗል
ዛሬ ፡ ለእኔ ፡ የዜማ ፡ ጊዜዬ ፡ ሆኗል

አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ (በተራዬ) (፪x)
ሌሊቱን ፡ በሚያነጋው ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ ፡ (ታብሷል) (፪x)
አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ (ይዤ ፡ ልምጣ) ፡ እኔም ፡ በተራዬ (፪x)
ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ በሚመጣው ፡ (በሚያነጋው) ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ (፪x)

ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ የምወጣበት ፡ እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ የምጭንበት
የጠላቴ ፡ አፍ ፡ የሚዘጋበት ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ የምከብርበት
ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ማልቀስ ፡ በሸለቆ ፡ የናሱም ፡ ደጃፍ ፡ ተበርግዷል ፡ አውቆ
ልሂድ ፡ ልውረሰው ፡ ከቶ ፡ አታዘግዩኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ውረሺው ፡ ያለኝ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ውረሺው ፡ ያለኝ (፬x)

በቃ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ተዘጋ
ጌታ ፡ ቀኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ አሻገረን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር
ማንኮራኩሩ ፡ ታስሮ ፡ ተጨነቀ ፡ ጠላቴ
እኔ ፡ ግን ፡ እየዘመርኩ ፡ ገባሁኝ ፡ ወደርስቴ

የማንም ፡ እምባ ፡ ባለዕዳ ፡ አይደለም ፡ ጌታ
ዘመናት ፡ ቆጥሮ ፡ ያቆማል ፡ በከፍታ (፪x)

ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡ ማህተሜን ፡ የፈታ (፬x)

አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ እኔም ፡ በተራዬ ፡ (በተራዬ) (፪x)
ሌሊቱን ፡ በሚያነጋው ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ ፡ (ታብሷል) (፪x)
አምልኮ ፡ ይዤ ፡ ልምጣ ፡ (ይዤ ፡ ልምጣ) ፡ እኔም ፡ በተራዬ (፪x)
ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ በሚመጣው ፡ (በሚያነጋው) ፡ ታብሷል ፡ እምባዬ (፪x)