እኔ ፡ የማምነው (Enie Yemamnew) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 2.jpg


(2)

ሰባሪው ፡ ጌታ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቷል
(Sebariw Gieta Kefitie Wettual)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

በዙሪያዬ ፡ ያለው ፡ ነገሬ ፡ ይህን ፡ ባይነግሬኝ
ነገርሽ ፡ ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ በቃ ፡ ብለኝ
አዲስ ፡ ነገር ፡ ማድረግ ፡ ሁልጊዜ ፡ ልማድ ፡ ያለው ፡ ጌታ
ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ይተጋል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ከፍታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)

አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x)

ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ
በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ
ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x)

በደረቁ ፡ አጥንቶች ፡ ነፍስን ፡ መዝራት
እንደ ፡ ሰው ፡ ሲታሰብ ፡ በምን ፡ ጉልበት
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ቀላል ፡ ነው
እጁ ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል ፡ ትልቅ ፡ ነው

ልጅ ፡ መውለድ ፡ በዘጠና ፡ ዓመት
ለሣራ ፡ ከባድ ፡ ነው ፡ ሲገመት
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለ ፡ ሆነ ፡ ነው
ታምር ፡ የሚሰራ ፡ ጌታ ፡ ነው [1]

እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
ኧረ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
ያልታሰበ ፡ ነገር ፡ ያደርጋል ፡ በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)
 
አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x)
 
ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ
በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ
ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x)

  1. ዘፍጥረት ፲፯ ፡ ፲፯ ፣ ፳፩ ፡ ፩ - ፭ (Genesis 17:17, 21:1-5)