እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ (Egziabhieren Barkiw Nefsie) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 2.jpg


(2)

ሰባሪው ፡ ጌታ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቷል
(Sebariw Gieta Kefitie Wettual)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ
እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው (፬x)

ውለታው ፡ ብዙ ፡ ነውና ፡ አብዢለት ፡ ምሥጋና (፬x)

ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የአንቺ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል
ልዑል ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አበሳሽን ፡ አርጐታል ፡ ገለል (፪x)

ሚስኪኑን ፡ ፍጹም ፡ ሳይረሳ ፡ ከአፈር ፡ ከትቢያ ፡ ሚያነሳ
የመርዶክዮስ ፡ አምላክ ፡ አርቋል ፡ የአንቺን ፡ አበሳ (፪x)

ፈቅደሽ ፡ አመስግኚው ፡ ያሰበሽ ፡ ጌታ ነው (፬x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ
እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው (፬x)

ውለታው ፡ ብዙ ፡ ነውና ፡ አብዢለት ፡ ምስጋና (፬x)

ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የአንቺ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል
ልዑል ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አበሳሽን ፡ አርጐታል ፡ ገለል (፪x)

በምህረቱ ፡ የከለለሽ ፡ ከበረከቱ ፡ ያጠገበሽ
በመከራሽ ፡ ቀን ፡ ያሰማሽ ፡ ፈቃድሽን ፡ የፈሰመልሽ (፪x)

ታዳጊሽ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ሥሙን ፡ ከፍ ፡ አድርጊው (፬x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው ፡ ነፍሴ
እግዚአብሔርን ፡ ባርኪው (፬x)

ውለታው ፡ ብዙ ፡ ነውና ፡ አብዢለት ፡ ምስጋና (፬x)

ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የአንቺ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል
ልዑል ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አበሳሽን ፡ አርጐታል ፡ ገለል (፪x)