From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ
እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
በወይን ፡ ሐረግ ፡ ዘንድ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
ባይኖር ፡ የሚረዳ ፡ ከግራ ፡ ከቀኝ
በለሷን ፡ ጠብቄ ፡ ፍሬን ፡ እበላለሁ
ቀኝ ፡ እጄን ፡ የያዘኝ ፡ መቼ ፡ ሊረሳኝ ፡ ነው
እሱን ፡ ታምኖ ፡ ጠርቶ ፡ ከቶ ፡ ማንስ ፡ አፍሯል
ይልቁን ፡ በስሙ ፡ ቀንዱ ፡ ከፍ ፡ ብሏል
እኔም ፡ በስሮቼ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ እላለሁ
አለኝ ፡ የሚረዳ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ (፫x)
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ
እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
ጨለማው ፡ በርትቶ ማይነጋ ሲመስል
ዮርዳኖስም ፡ ሞልቶ ፡ አላሻግርም ፡ ሲል
ታምራት ፡ አድርጎ ፡ ያሻገረው ፡ ጌታ
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ በእኔ ፡ ቦታ
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ድል ፡ የነሳ ፡ ጌታ
ሰባቱን ፡ ማህተም ፡ ተርትሮ ፡ የፈታ
ዛሬም ፡ በቸርነት ፡ ይከታተለኛል
እሱን ፡ ተደግፌ ፡ ምንስ ፡ ያሰጋኛል (፫x)
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ
እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x)
ወረት ፡ የለበትም ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሌ ፡ ስያፈቅር ፡ ይኖራል
መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጉዞ ፡ መች ፡ እዚህ ፡ አውጥቶ ፡ ይሄዳል
እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ አርጎ ፡ ይዞ ፡ በብዙ ፡ ሞገስ ፡ ያኖራል
ላይተው ፡ ላይረሳ ፡ በራሱ ፡ በስሙ ፡ ኪዳን ፡ ይምላል (፪x)
|