ነውር ፡ ነው (Newere New) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Lyrics.jpg


(4)

አልበም
(Album 4)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ሠው ይታመን የለም ወይ በሚያልፈው በሚጠፋው
እንኳን በነገስታት ንጉስ ዘላለሜን በያዘው
ሠው ይደገፍ የለም ወይ ተሠብሮ በሚወጋው
እንኳን ጨለማን ገፎ በህይወት በሚያኖረው----(2X)

እስኪ ተነስቼ ችግሬ ላይ ልፎክርበት
እስኪ ተነስቼ ተራራው ላይ ልዘምርበት
እስኪ ተነስቼ ዬርዳኖስ ላይ ቃል ልምዘዝበት
እስኪ ተነስቼ ጎልያድ ላይ ልጓደድበት

ነውር ችግር አይፈራም እኔ ቤት
ነውር ችግር አይፈራም እኔ ቤት (6X)

እስኪ ተነስቼ ችግሬ ላይ ልፎክርበት
እስኪ ተነስቼ ተራራው ላይ ልዘምርበት
እስኪ ተነስቼ ዬርዳኖስ ላይ ቃል ልምዘዝበት
እስኪ ተነስቼ ጎልያድ ላይ ልጏደልበት

ነውር ችግር አይፈራም እኔ ቤት
ነውር ችግር አይፈራም እኔ ቤት (6X)

ዞርበል ከኔ ጋር ዞር በል ጥፋ ተራዬ ነው
ንጉስ ተነስቶ እኔ ስቀመጥ በብዙ ነውር ነው
ነግቷል እያለኝ የምን ጭለማ የምንስ ሟርት ነው
ይልቅ ልነሳ ወገቤን ላጥብቅ ዱሩን ልመንጥረው----(6X)

ሞቶብኝ አይደለም ተኝቶ እንጂ ተኝቶ ነው እንጂ
ሚስጥሩን ነገረኝ ያ የኔ ወዳጅ ያ የኔ ወዳጂ
ሠላም ነው ገና ነው ልበል በመዝሙሬ ልበል በመዝሙሬ
እሻገር የለም ወይ ተሠርቶ ነገሬ ተሠርቶ ነገሬ

በፊትህ ልውጣ በከበሮ ታማኝ ነው ጌታ በቀጠሮ
መች አስጠብቆኝ ቀርቶ ያውቃል ሁሉንም ደህና ያደርገዋል
በደመናት ላይ ለረድኤቴ ስሔድ ያየሁት መድሀኒቴ
አልተለወጠም ዛሬም ያው ነው ሁሌም ይሠራል አምነዋለው

ዞርበል ከኔ ጋር ዞር በል ጥፋ ተራዬ ነው
ንጉስ ተነስቶ እኔ ስቀመጥ በብዙ ነውር ነው
ነግቷል እያለኝ የምን ጭለማ የምንስ ሟርት ነው
ይልቅ ልነሳ ወገቤን ላጥብቅ ዱሩን ልመንጥረው----(2X)

የሌለውን ጠርቶ በድል ሲያኖረኝ በድል ሲያኖረኝ
ጊንጡን ተሸክሞ እሽኮኮ ሲለኝ እሽኮኮ ሲለኝ
እያየሁኝ ኖረ ስንቱን ተአምር ስንቱን ተአምር
እንዴት ልቤ ይፍራ ለምን ልሸበር ለምን ልሸበር

በበረሀ ውስጥ እያወጣ ምንጭን ከአለት እያጠጣ
ባህርን ከፍሎ ያሻገረኝ እግዚአብሔር አለ የከበረ
እሱን ታምኜ ተደግፌ እንደ ንስር በክንፍ አልፌ
እበረታለው እወርሳለው ከቶ አልታክትም ከፍ እላለው

ዞርበል ከኔ ጋር ዞር በል ጥፋ ተራዬ ነው
ንጉስ ተነስቶ እኔ ስቀመጥ በብዙ ነውር ነው
ነግቷል እያለኝ የምን ጭለማ የምንስ ሟርት ነው
ይልቅ ልነሳ ወገቤን ላጥብቅ ዱሩን ልመንጥረው----(2X)


https://www.youtube.com/watch?v=RK1FeOkxyXw