ከአንተ ፡ ወዴት (Kante Wedet) - አዲስዓለም ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዲስዓለም ፡ አሰፋ
(Addisalem Assefa)

Addisalem Assefa 3.jpg


(3)

ጆሮዬን ልብሳ
(Joroyen Libsa)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዲስዓለም ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Addisalem Assefa)

ካንተ ወዴት እሄዳለው
ካንተ ወደ ማን እሄዳለው
2x

የሱስ ህይወቴን አድነህ
ባንተ መሞት ሰው ሆኛለሁ
ከጥላህ በታች አርፌ
ፍቅርህን ቀምሼዋለሁ
2x

አመሰግንሃለሁ 4x
ምስጋናዬ ስምህን ያክብረው
እልልታዬ ማደሪያህን ይሙላው
2x

የምትበላ የህይወት እንጀራ
ድኜ ቀረሁኝ ስምህን ስጠራ 2x
ሮጬ አመለጥኩኝ ከመከራዬ
ልዘምር መጣሁ ተከፍሎ ዕዳዬ
ልዘምር መጣሁ ታብሶ ዕምባዬ

አዝ፦ እስትንፋሴ የመኖሬ ህልውና
አንተኮ ነህ የቤቴ ራስ ገናና
ዝና ክብሬ ደም ግባቴ ሞገሴ
ይኸው መጣሁ ልሰግድልህ እየሱሴ
እንካ ክብሬን እንካ አምልኮዬን
የሚገባው ላንተ ነው
ሰው ያደረገኝ ደምህ/ልጅህ ነው 2x

በመስቀል ጣርህ የወለድከኝ
ከሲዖል ነጥቀህ ያወጣኸኝ 2x
የልቤን ኃጥያት የተወክልኝ
በብዙ ምህረት የከበብከኝ
በጥንቃቄ ያሳደከኝ

አዝ፦ እስትንፋሴ የመኖሬ ህልውና
አንተኮ ነህ የቤቴ ራስ ገናና
ዝና ክብሬ ደም ግባቴ ሞገሴ
ይኸው መጣሁ ልሰግድልህ እየሱሴ
እንካ ክብሬን እንካ አምልኮዬን
የሚገባው ላንተ ነው
ሰው ያደረገኝ ደምህ/ልጅህ ነው 2x

ካንተ ወዴት እሄዳለው
ካንተ ወደ ማን እሄዳለው
2x

የሱስ ህይወቴን አድነህ
ባንተ መሞት ሰው ሆኛለሁ
ከጥላህ በታች አርፌ
ፍቅርህን ቀምሼዋለሁ
2x